ኢሳይያስ 48:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዘርህም እንደ አሸዋ የሆድህም ትውልድ እንደ ምድር ትቢያ በሆነ ነበር፥ ስሙም ከፊቴ ባልጠፋና ባልፈረሰ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዘርህ እንደ አሸዋ፣ ልጆችህ ስፍር እንደሌለው ትቢያ በሆኑ ነበር፤ ስማቸው አይወገድም፤ ከፊቴም አይጠፋም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝባችሁም ባልተደመሰሰና ስማችሁም ባልተረሳ ነበር!” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዘርህም እንደ አሸዋ የሆድህም ትውልድ እንደ ምድር ትቢያ በሆነ ነበር፤ አሁንም ስምህ ከፊቴ ባልጠፋና ባልፈረሰ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዘርህም እንደ አሸዋ የሆድህም ትውልድ እንደ ምድር ትቢያ በሆነ ነበር፥ ስሙም ከፊቴ ባልጠፋና ባልፈረሰ ነበር። |
በእውነት መባረክን እባርክሃለሁ፥ ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብት እና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ አበዛዋለሁ፤ ዘሮችህም የጠላቶችን ደጅ ይወርሳሉ፥
እስራኤላውያንን ከሰጠኋቸው ምድር ተነቃቅለው እንዲባረሩ አደርጋለሁ፤ ስሜ እንዲጠራበት የቀደስኩትንም ይህን ቤተ መቅደስ እተወዋለሁ፤ በየአገሩ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ እስራኤልን መሳለቂያና መዘባበቻ ያደርጓታል።
የሰማይን ሠራዊት መቁጠር የባሕርንም አሸዋ መስፈር እንደማይቻል፥ እንዲሁ የባርያዬን የዳዊትን ዘርና የሚያገለግሉኝን ሌዋውያንን አበዛለሁ።”
እጄንም በይሁዳ ላይና በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ሁሉ ላይ እዘረጋለሁ፥ ከዚህም ስፍራ የበዓልን ትሩፍና የጣዖታቱን ካህናት ስም ከካህናቱ ጋር እቆርጣለሁ፤
ደግሞም የምዋቹ ስም ከወንድሞቹ መካከል ከአገሩም ደጅ እንዳይጠፋ፥ የምዋቹን ስም በርስቱ ላይ እንዳስነሣ የመሐሎንን ሚስት ሞዓባዊቱን ሩትን ሚስት ትሆነኝ ዘንድ ወሰድሁአት፥ እናንተም ዛሬ ምስክሮች ናችሁ” አላቸው።