ኢሳይያስ 44:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጠራቢው ገመድ ይዘረጋል፥ በጠመኔም ምልክት ያኖራል፥ በመሮም ይቀርጸዋል፥ በመለኪያም ይለከዋል፤ በቤትም ውስጥ እንዲቀመጥ በሰው አምሳልና በሰው ውበት ይቀርጸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእጅ ጥበብ ባለሙያ በገመድ ይለካል፤ በጠመኔ ንድፍ ያወጣል፤ በመሮ ይቀርጸዋል፤ በጸርከል ምልክት ያደርግበታል። በሰው አምሳል ይቀርጸዋል፤ የሰውንም ውበት ያለብሰዋል፤ በማምለኪያም ስፍራ ያስቀምጠዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አናጢ በእንጨቱ ላይ መስመርን ያሰምራል፤ ንድፍም ይነድፋል፤ በመላጊያ ያለሰልሰዋል፤ በማስተካከያ መሣሪያም ትክክልነቱን ያረጋግጣል፤ ውበት ያለው የሰው ቅርጽ እንዲኖረው ያደርጋል። ከዚያም በጣዖት ቤት ያኖረዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠራቢውም እንጨት ቈርጦ በልኩ ያቆመዋል፤ በማጣበቂያም ያያይዘዋል፤ በሰው አምሳልና በሰው ውበት ያስመስለዋል፤ በቤትም ውስጥ ያቆመዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጠራቢውም ገመድ ይዘረጋል በበረቅም ያመለክተዋል በመቅረጫም ይቀርጸዋል በመለኪያም ይለከዋል፥ በቤትም ውስጥ ይቀመጥ ዘንድ በሰው አምሳልና በሰው ውበት ያስመስለዋል። |
አምላኮችህን የምታገኝበት ሰው ግን እርሱ ይሙት፥ የአንተ የሆነውም በእኔ ዘንድ ይገኝ እንደሆነ በዘመዶቻችን ፊት ፈልግ፥ ውሰደውም” አለ። ያዕቆብ ራሔል እንደ ሰረቀቻቸው አያውቅም ነበር።
ስለዚህ ያዕቆብ ለቤተሰቡና ከእርሱ ጋር ላሉት ሁሉ እንዲህ አለ፦ “እንግዶቹን አማልክት ከመካከላችሁ አስወግዱ ንጹሐንም ሁኑ፥ ልብሳችሁንም ለውጡ፥
አናጢውም አንጥረኛውን፥ በመዶሻም የሚያሳሳውን በመስፍ ላይ የሚቀጠቅጠውን ያጽናናዋል፥ ስለ ብየዳ ሥራውም፦ “መልካም ነው” ይለዋል፤ እንዳይላቀቅም በችንካር ያጋጥመዋል።
የዝግባን ዛፎች ይቈርጣል፤ የዞጲንና የኮምቦልን ዛፍ ይመርጣል፥ ከዱር ዛፎችም መካከል እንዲጠነክር ይተወዋል፤ የጥድንም ዛፍ ይተክላል፥ ዝናብም ያበቅለዋል።
እኔም ገባሁና አየሁ፥ እነሆ የሁሉም ዓይነት የሚሳቡ ነገሮች፥ የርኩሳን እንስሶች ምስሎችና የእስራኤል ቤት ጣዖታት ሁሉ በግንቡ ዙሪያ ተስለው ነበር።
ከእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች ሰባ ሰዎች ቆመው ነበር፥ የሻፋን ልጅ ያአዛንያ በመካከላቸው ቆሞ ነበር፥ እያንዳንዱም በእጁ ጥናውን ይዞ ነበር፥ መልካም መዓዛ ያለው የዕጣኑም ጢስ ወደ ላይ ይወጣ ነበር።
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች እያንዳንዱ በስዕሉ ቤት በጨለማ የሚያደርጉትን አይተሃልን? እነርሱም፦ “ጌታ አያየንም፥ ጌታ ምድሪቱን ትቶአታል፥ ብለዋልና።”
እንግዲህ የእግዚአብሔር ዘመዶች ከሆንን፥ አምላክ በሰው ብልሃትና አሳብ የተቀረጸውን ወርቅ ወይም ብር ወይም ድንጋይ እንዲመስል እናስብ ዘንድ አይገባንም።
የማይጠፋውን የእግዚአብሔርን ክብር በሚጠፋው በሰው፥ በወፎች፥ አራት እግር ባላቸው እንስሳትና በመሬት ላይ በሚሳቡ እንስሳት መልክ ምስል ለወጡ።
“‘በጌታ ዘንድ የተጠላ የሠራተኛ እጅ ሥራን የተቀረጸ ወይም ቀልጦ የተሠራ ምስልን የሚያደርግ፥ በስውርም የሚያቆመው ሰው የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል።
እርሱም፥ “እንዴት፥ ‘ምን ሆንክ’ ብላችሁ ትጠይቁኛላችሁ? የሠራኋቸውን አማልክቴንና ካህኔን ወስዳችሁ ሄዳችኋል፤ ምን የቀረኝ ነገር አለ?” አላቸው።