ኢሳይያስ 43:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብ ሆይ፥ አንተ ግን አልጠራኸኝም፥ አንተም እስራኤል ሆይ፥ በእኔ ዘንድ ደክመሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ያዕቆብ ሆይ፤ አንተ ግን አልጠራኸኝም፤ እስራኤል ሆይ፤ የእኔ ነገር ታክቶሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል! “የያዕቆብ ልጆች እስራኤላውያን ሆይ፥ እናንተ ስሜን መጥራት ትታችኋል፤ ልታገለግሉኝም አልፈለጋችሁም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብ ሆይ፥ እነሆ፥ አልጠራሁህም፤ አንተም እስራኤል ሆይ፥ አልዘበዘብሁህም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብ ሆይ፥ አንተ ግን አልጠራኸኝም፥ አንተም እስራኤል ሆይ፥ በእኔ ዘንድ ደክመሃል። |
ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፥ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል፥ በደላችንም እንደ ነፋስ ወስዶናል።
ያዕቆብን በልተውታልና፥ ውጠውታልምና፥ አጥፍተውታልምና፥ ማደሪያውንም አፍርሰዋልና በማያውቁህ አሕዛብ ስምህንም በማይጠሩ ወገኖች ላይ መዓትህን አውርድ።
“እነሆ፥ ይህ ድካም ነው ብላችሁ ጢቅ አላችሁበት፥” ይላል የሠራዊት ጌታ፤ “የተሰረቀውን፥ አንካሳውንና የታመመውን አምጥታችኋል፤ እንዲሁም ቁርባንን አምጥታችኋል፤ በውኑ ከእጃችሁ መቀበል ይገባኛልን?” ይላል ጌታ።
በቃላችሁ ጌታን አሰልችታችሁታል። እናንተም፦ እርሱን ያሰለቸነው በምንድን ነው? ትላላችሁ። “ክፉን የሚያደርግ ሁሉ በጌታ ፊት መልካም ነው፥ እርሱም በእነርሱ ደስ ይለዋል” ወይም “የፍትሕ አምላክ የት አለ?” በማለታችሁ ነው።
እናንተም እንዲህ ብላችኋል፦ እግዚአብሔርን ማገልገል ከንቱ ነው፤ ትእዛዙን መጠበቅ፥ በሠራዊት ጌታ ፊት ኀዘንተኞች ሆነን መሄድ ምን ይጠቅመናል?