ኢሳይያስ 43:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተናግሬአለሁ፥ አድኛለሁ፥ አሳይቻለሁ፥ በእናንተም ዘንድ ባዕድ አምላክ አልነበረም፤ ስለዚህ እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ፥ ይላል ጌታ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ገልጫለሁ፤ አድኛለሁ፤ ተናግሬአለሁ፤ በመካከላችሁ እኔ እንጂ ባዕድ አምላክ አልነበረም። እኔ አምላክ እንደ ሆንሁ፣ እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ወደፊት የሚሆነውን ነገር አስቀድሜ ተናግሬአለሁ፤ እናንተን ያዳንኩ እኔ ነኝ፤ ከባዕዳን አማልክት አንድ እንኳ ይህን አላደረገም፤ ለዚህ ሁሉ እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተናግሬአለሁ፤ አድኜማለሁ፤ መክሬማለሁ፤ በእናንተም ዘንድ ባዕድ አምልኮ አልነበረም፤ ስለዚህ እኔ እግዚአብሔር አምላክ እንደ ሆንሁ እናንተ ራሳችሁ ምስክሮች ናችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተናግሬአለሁ አድኜማለሁ አሳይቼማለሁ፥ በእናንተም ዘንድ ባዕድ አምላክ አልነበረም፥ ስለዚህ እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እኔም አምላክ ነኝ። |
እነሆ፥ በላዩ መንፈስን እሰድዳለሁ፥ ወሬም ይሰማል፥ ወደ ምድሩም ይመለሳል፤ በምድሩም ላይ በሰይፍ እንዲወድቅ አደርጋለሁ በሉት’ ” አላቸው።
ታውቁና ታምኑብኝ ዘንድ እኔም እንደሆንሁ ታስተውሉ ዘንድ፥ እናንተ የመረጥሁትም አገልጋዬ ምስክሮቼ ናችሁ ይላል ጌታ፤ ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም ከእኔም በኋላ አይኖርም።
አትፍሩ አትደንግጡም፤ ከጥንቱም ጀምሬ አልነገርኋችሁም? ወይስ አላሳየኋችሁም? እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ። ከእኔ ሌላ አምላክ አለን? ሌላ ዐለት የለም፤ አንድም አላውቅም።
በስውር ወይም በጨለማ ምድር አልተናገርሁም፤ ለያዕቆብ ዘር፦ በከንቱ ፈልጉኝ አላልሁም፤ እኔ ጌታ እውነትን እናገራለሁ ትክክለኛውንም አወራለሁ።
“እኔ ራሴ እርሱ እንደሆንሁ እዩ፤ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ እኔ እገድላለሁ፤ በሕይወትም አኖራለሁ፤ እኔ አቆስላለሁ፤ እፈውሳለሁም፤ ከእጄም የሚያስጥል ማንም የለም።