La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢሳይያስ 41:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በመጀመሪያ ለጽዮን፦ እነሆ ተመልከች፥ እላለሁ፤ ለእየሩሳሌምም የምሥራች ነጋሪን እሰጣለሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በመጀመሪያ፣ ‘እነሆ፤ ተመልከቺአቸው!’ ብዬ ለጽዮን የተናገርሁ እኔ ነበርሁ፤ ለኢየሩሳሌምም የምሥራች ነጋሪን ሰጥቻለሁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በመጀመሪያ ይህን ዜና ለጽዮን የገለጥኩላት እኔ ነኝ፤ ለኢየሩሳሌምም መልካም ዜና አብሣሪ የላክሁላት እኔ ነኝ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በመ​ጀ​መ​ሪያ ለጽ​ዮን፦ ግዛ​ትን እሰ​ጣ​ታ​ለሁ፤ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ወደ መን​ገ​ድዋ እመ​ል​ሳ​ታ​ለሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በመጀመሪያ ለጽዮን፦ እነኋቸው እላለሁ፥ ለእየሩሳሌምም የምስራች ነጋሪን እሰጣለሁ።

Ver Capítulo



ኢሳይያስ 41:27
14 Referencias Cruzadas  

የምሥራች የምትነግሪ ጽዮን ሆይ፥ ከፍ ወደለው ተራራ ውጪ፤ የምሥራች የምትነግሪ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ድምፅሽን በኃይል አንሺ፤ አንሺ፥ አትፍሪ፤ ለይሁዳም ከተሞች፦ እነሆ፥ አምላካችሁ! ብለሽ ንገሪ።


ይህን የሠራና ያደረገ፥ ትውልድንም ከጥንት የጠራው ማን ነው? እኔ ጌታ፥ መጀመሪያም እስከ መጨረሻውም የምኖር፥ እኔ ነኝ።


ታውቁና ታምኑብኝ ዘንድ እኔም እንደሆንሁ ታስተውሉ ዘንድ፥ እናንተ የመረጥሁትም አገልጋዬ ምስክሮቼ ናችሁ ይላል ጌታ፤ ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም ከእኔም በኋላ አይኖርም።


ቂሮስንም፦ “እርሱ እረኛዬ ነው”፤ እርሱም ኢየሩሳሌምን፦ “ትታነጺያለሽ ቤተ መቅደስም ይመሠረታል” ይላል፤ እኔም “ፈቃዴን ሁሉ ይፈጽማል” እላለሁ።


የእስራኤል ንጉሥ ጌታ፥ የሚቤዥም የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እኔ ፊተኛ ነኝ፥ እኔ ፍጻሜም ነኝ፤ ከእኔ ሌላም አምላክ የለም።


እኔ አምላክ ነኝና፥ ሌላም የለምና የቀድሞውን የጥንቱን ነገር አስቡ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ እንደ እኔም ያለ ማንም የለም።


ያዕቆብ ሆይ፥ የጠራሁህም እስራኤል ሆይ፥ ስማኝ፤ እኔ ነኝ፤ እኔ ፊተኛው ነኝ እኔም ኋለኛው ነኝ።


የቀድሞውን ነገር ከጥንት ተናግሬአለሁ፥ ከአፌም ወጥቶአል፥ አሳይቼውማለሁ፤ ድንገት አድርጌው ተፈጽሞዋል።


የምሥራች የሚናገር፥ ሰላምንም የሚያወራ፥ የመልካምንም ወሬ የምሥራች የሚናገር፥ መድኃኒትንም የሚያወራ፥ ጽዮንንም፦ አምላክሽ ነግሦአል የሚል ሰው እግሩ በተራሮች ላይ እጅግ ውብ ነው።


ካልተላኩስ እንዴት ይሰብካሉ? “መልካሙን ዜና የሚያበሥሩ እግሮቻቸው እንዴት ውብ ናቸው!” ተብሎ እንደተጻፈው ነው።


“በሰምርኔስም ወዳለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፥ ሞቶ የነበረው፥ ሕያውም የሆነው፥ ፊተኛውና መጨረሻው እንዲህ ይላል፦