እድናውቀው ከጥንት የተናገረው፦ እውነት ነው፥ እንድንልም ቀድሞ የተናገረው ማን ነው? የሚናገር የለም፥ የሚገልጥም የለም፥ ቃላችሁንም የሚሰማ የለም።
ኢሳይያስ 41:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያምጡ፥ የሚሆነውንም ይንገሩን፤ ልብም እድናደርግ፥ ፍጻሜአቸውንም እድናውቅ፥ የቀደሙት ነገሮች ምን እንደ ሆኑ ተናገሩ፥ የሚመጡትንም አሳዩን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የሚሆነውን እንዲነግሩን፣ ጣዖቶቻችሁን አምጡ፤ እንድንገነዘብ፣ ፍጻሜአቸውን እንድናውቅ፣ የቀደሙት ነገሮች ምን እንደ ነበሩ ንገሩን፤ ስለሚመጡትም ነገሮች ግለጹልን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጣዖቶቻችሁንም አምጡና በሚፈጸምበት ጊዜ እንድናውቀው ወደ ፊት የሚሆነውን ሁሉ እስቲ ይንገሩን፤ ወደፊት ውጤታቸው ምን እንደሚሆን አስተውለን እንረዳ ዘንድ የቀድሞዎቹ ነገሮች ምን እንደ ሆኑ ይንገሩን፤ ወይም ወደፊት ምን እንደሚከሠት ያስረዱን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይምጡ፤ የሚደርስባችሁንም ይንገሩን፤ ልብም እናደርግ ዘንድ፤ ፍጻሜአቸውንም እናውቅ ዘንድ፥ የቀደሙት ነገሮች ምን እንደ ሆኑ ንገሩን፤ የሚመጡትንም አሳዩን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያምጡ፥ የሚሆነውንም ይንገሩን፥ ልብም እናደርግ ዘንድ ፍጻሜአቸውንም እናውቅ ዘንድ፥ የቀደሙት ነገሮች ምን እንደሆኑ ተናጋሩ፥ የሚመጡትንም አሳዩን። |
እድናውቀው ከጥንት የተናገረው፦ እውነት ነው፥ እንድንልም ቀድሞ የተናገረው ማን ነው? የሚናገር የለም፥ የሚገልጥም የለም፥ ቃላችሁንም የሚሰማ የለም።
ይናገሩ ይቅረቡም በአንድነትም ይማከሩ፤ ከጥንቱ ይህን ያሳየ ከቀድሞስ የተናገረ ማን ነው? ያሳየሁም የተናገርሁም እኔ ጌታ አይደለሁምን? ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ እኔ ጻድቅ አምላክና መድኃኒት ነኝ፥ ከእኔም በቀር ማንም የለም።
እናንተ ሁሉ፥ በአንድነት ተሰብስባችሁ ስሙ፤ ከእነርሱ ይህን የተናገረ ማን ነው? ጌታ የወደደው ፈቃዱን በባቢሎን ላይ ያደርጋል፥ ክንዱም በከለዳውያን ላይ ይሆናል።