እነዚህም አገልጋዮችህ ሁሉ ወደ እኔ ይወርዳሉ፥ ለእኔም ይሰግዳሉ፥ ‘አንተ ውጣ በሥርህ ያለ ሕዝብ ሁሉ ይውጣ’ ይላሉ፤ ከዚያም በኋላ እወጣለሁ።” ሙሴም በጽኑ ቁጣ ከፈርዖን ዘንድ ወጣ።
ኢሳይያስ 41:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ የሚቆጡህ ሁሉ ያፍራሉ፥ ይዋረዳሉም፤ የሚከራከሩህም እንዳልነበሩ ይሆናሉ፥ ይጠፋሉም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እነሆ፤ የተቈጡህ ሁሉ፣ እጅግ ያፍራሉ፤ ይዋረዳሉም፤ የሚቋቋሙህ፣ እንዳልነበሩ ይሆናሉ፤ ይጠፋሉም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአንተ ላይ የተቈጡ ሁሉ ተሸንፈው ያፍራሉ፤ አንተንም ለመጒዳት የሚነሡ ጠፍተው እንዳልነበሩ ይሆናሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ የሚቃወሙህ ሁሉ ያፍራሉ፤ ይዋረዱማል፤ እንዳልነበሩም ይሆናሉ፤ ጠላቶችህም ይጠፋሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ የሚቆጡህ ሁሉ ያፍራሉ፥ ይዋረዱማል፥ የሚከራከሩህም እንዳልነበሩ ይሆናሉ፥ ይጠፉማል። |
እነዚህም አገልጋዮችህ ሁሉ ወደ እኔ ይወርዳሉ፥ ለእኔም ይሰግዳሉ፥ ‘አንተ ውጣ በሥርህ ያለ ሕዝብ ሁሉ ይውጣ’ ይላሉ፤ ከዚያም በኋላ እወጣለሁ።” ሙሴም በጽኑ ቁጣ ከፈርዖን ዘንድ ወጣ።
እንዲህም ሆነ እኩለ ሌሊት ላይ ጌታ በግብጽ ምድር ያለውን በኩር ሁሉ፥ በዙፋን ከተቀመጠው ከፈርዖን በኩር ጀምሮ በእስር ቤት እስካሉት እስከ እስረኞች በኩር ድረስ፥ የከብቶችንም በኩር ሁሉ መታ።
ሕዝቦች እንደ ብዙ ውኃ ጩኸት ይጮኻሉ፤ እርሱ ግን ይገሥጻቸዋል፤ እነርሱም እየሸሹ ይርቃሉ፤ በተራራም ላይ እንዳለ እብቅ በነፋስ ፊት፥ ዐውሎ ነፋስ እንደሚያዞረውም ትቢያ ይበተናሉ።
ተርቦም እንደሚያልም ሰው ይሆናል፤ በሕልሙም፥ እነሆ፥ ይበላል፥ ነገር ግን ይነቃል ሰውነቱም ባዶ ነው፤ ተጠምቶም እንደሚያልም ሰው ይሆናል፤ በሕልሙም፥ እነሆ፥ ይጠጣል፥ ነገር ግን ይነቃል፥ እነሆም፥ ይዝላል ሰውነቱም እንደተጠማ አለ፤ የጽዮንን ተራራም የሚወጉ የአሕዛብ ሁሉ ብዛት እንደዚሁ ይሆናል።
ለኢየሩሳሌም ልብ ተናገሩ፤ የተቀጠረችበት ወራት እንደ ተፈጸመ፥ ኃጢአትዋም እንደ ተሰረየ፥ ከጌታም እጅ ስለ ኃጢአትዋ ሁሉ ሁለት እጥፍ እንደ ተቀበለች ወደ እርሷ ጩኹ።
ጌታ ግን እንዲህ ይላል፦ ከአንቺ ጋር የሚጣሉትን እጣላቸዋለሁ፥ ልጆችሽንም አድናለሁና፥ በኃያላን የተማረኩ እንኳን ይወሰዳሉ፥ የጨካኞች ብዝበዛም ቢሆን ያመልጣል።
አስጨናቂዎችሽንም ሥጋቸውን አስበላቸዋለሁ፥ እንደ ጣፋጭም ወይን ጠጅ ደማቸውን ጠጥተው ይሠክራሉ፤ ሥጋ ለባሹም ሁሉ እኔ ጌታ መድኃኒትሽና ታዳጊሽ፥ የያዕቆብ ኃያል እንደሆንሁ ያውቃል።
በአንቺ ላይ የተሠራ መሣሪያ ሁሉ አይከናወንም፤ በፍርድም የሚነሣብሽን ምላስ ሁሉ ትፈርጂበታለሽ። የጌታ አገልጋዮች ርስት ይህ ነው፥ ጽድቃቸውም ከእኔ ዘንድ ነው፥ ይላል ጌታ።
እስራኤል ለጌታ ቅዱስ ነበረ፥ የአዝመራውም በኵራት ነበረ፤ የበሉት ሁሉ እንደ በደለኞች ይቈጠራሉ፥ ክፉም ነገር ይመጣባቸዋል፥ ይላል ጌታ።”
በዚያም ቀን ኢየሩሳሌምን ለአሕዛብ ሁሉ ከባድ ድንጋይ አደርጋታለሁ፤ የምድርም አሕዛብ ሁሉ ሊያጠቋት ቢሰበሰቡም፥ ሊያነሷት የሚሞክሩ ሁሉ ራሳቸውን እጅግ ይጎዳሉ።
እነሆ አይሁድ ሳይሆኑ ‘አይሁድ ነን’ ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ፤ እነሆ መጥተው በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ።