ኢሳይያስ 40:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሕዛብ ሁሉ በፊቱ እንዳልነበሩ ናቸው፤ ከምንም እንደሚያንሱ፥ እንደ ባዶ ነገር ይቈጠራሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሕዛብ ሁሉ በፊቱ እንደ ኢምንት ናቸው፤ ከምንም የማይቈጠሩ መና ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእግዚአብሔር ዘንድ ሕዝቦች ሁሉ እንዳሉ የሚቈጠሩ አይደሉም። እነርሱ በእርሱ ዘንድ እንደ ኢምንት የሚቈጠሩና ዋጋ የሌላቸው ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሕዛብ ሁሉ በፊቱ እንዳልነበሩ ናቸው፤ እንደ ከንቱ ነገርም ይመስላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አህዛብ ሁሉ በፊቱ እንዳልነበሩ ናቸው፥ ከምናምን እንደሚያንሱ፥ እንደ ከንቱ ነገርም ይቈጥራቸዋል። |
በመመካቴ ሞኝ ሆኜአለሁ! ይህ እናንተ ግድ ስላላችሁኝ የሆነ ነው። እኔ ከምንም የማልቆጠር ብሆን እንኳን፥ ከዋነኞቹ ሐዋርያት በምንም አላንስምና፥ በእርግጥም እናንተ ስለ እኔ መናገር ይገባችሁ ነበር።