ኢሳይያስ 38:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሲኦል አያመሰግንህምና፥ ሞትም አያከብርህምና፤ ወደ ጉድጓዱ የሚወርዱ እውነትህን ተስፋ አያደርጉም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሲኦል አያመሰግንህም፤ ሞት አያወድስህም፤ ወደ ጕድጓድ የሚወርዱ፣ የአንተን ታማኝነት ተስፋ አያደርጉም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሙታን ዓለም ሊያመሰግንህ የሚችል አንድ እንኳ የለም፤ ሙታንም ሊያመሰግኑህ አይችሉም፤ ወደ መቃብር የወረዱትም ታማኝነትህን ተስፋ አያደርጉም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመቃብር የሚኖሩ አያመሰግኑህምና፤ ሙታንም የሚያመሰግኑህ አይደሉምና፤ በሲኦልም የሚኖሩ ይቅርታህን ተስፋ አያደርጉምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሲኦል አያመሰግንህምና፥ ሞትም አያከብርህምና፥ ወደ ጕድጓዱ የሚወርዱ እውነትህን ተስፋ አያደርጉም። |