La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢሳይያስ 37:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የአሦርም ንጉሥ፦ “የኢትዮጵያ ንጉሥ ቲርሐቅ ሊዋጋህ መጥቷል” የሚል ወሬ ሰማ። ይህን በሰማም ጊዜ ወደ ሕዝቅያስ መልእክተኞችን ላከ፥ እንዲህም አለው፦

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ደግሞም ሰናክሬም፣ የኢትዮጵያ ንጉሥ ቲርሐቅ ሊወጋው መምጣቱን ሰማ፤ ይህንም እንደ ሰማ ወደ ሕዝቅያስ መልእክተኞች ላከ፤ እንዲህም አለ፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በኢትዮጵያ ንጉሥ በቲርሃቃ የሚመራ የግብጽ ሠራዊት እነርሱን ለመውጋት በመገሥገሥ ላይ መሆኑን አሦራውያን ሰሙ፤ የአሦር ንጉሥ ይህን በሰማ ጊዜ ወደ ሕዝቅያስ እንዲህ የሚል ደብዳቤ በመልእክተኛ እጅ ላከ፦

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እር​ሱም፥ “የኢ​ት​ዮ​ጵያ ንጉሥ ቲር​ሐቅ ሊዋ​ጋህ መጥ​ቶ​አል” የሚል ወሬ ሰማ። በሰ​ማም ጊዜ ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ እን​ዲህ ሲል፦

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እርሱም፦ የኢትዮጵያ ንጉሥ ቲርሐቅ ሊዋጋህ መጥቶአል የሚል ወሬ ሰማ። በሰማም ጊዜ ወደ ሕዝቅያስ መልእክተኞችን ላከ፥ እንዲህ ሲል፦

Ver Capítulo



ኢሳይያስ 37:9
7 Referencias Cruzadas  

ከዚህም በኋላ ንጉሥ ቤንሀዳድ በከተማይቱ ወደሚገኘው ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ አክዓብ፥ “ቤንሀዳድ እንዲህ ይላል ብሎ መልእክተኞችን ላከ፦


ለሕዝቡም መልእክተኞች ምን ብሎ መልስ ይሰጣል? “ጌታ ጽዮንን መሥርቷል፥ ከሕዝቡም ችግረኞች በእርሷ ውስጥ መጠጊያን ያገኛሉ።”


በኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ ላለች፥ ክንፍ ያላቸው መርከቦች ላሉባት፥


ጌታም እንዲህ አለ፦ “አገልጋዬ ኢሳይያስ በግብጽና በኢትዮጵያ ላይ ሦስት ዓመት ለምልክትና ለተአምራት እንዲሆን ራቁቱንና ባዶ እግሩን እንደ ሄደ፥


እነርሱም ከተስፋቸው ከኢትዮጵያ ከትምክሕታቸውም ከግብጽ የተነሣ ይፈራሉ፤ ያፍራሉም።


እነሆ፥ በላዩ መንፈስን እሰድዳለሁ፥ ወሬም ይሰማል፥ ወደ ምድሩም ይመለሳል፤ በምድሩም ላይ በሰይፍ እንዲወድቅ አደርጋለሁ በሉት’ ” አላቸው።