La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢሳይያስ 37:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ራፋስቂስም ተመለሰ፤ የአሦርም ንጉሥ ከለኪሶ እንደ ራቀ ሰምቶ ስለ ነበር በልብና ከተማ ሲዋጋ አገኘው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የጦር አዛዡም፣ የአሦር ንጉሥ ለኪሶን ትቶ መሄዱን ሲሰማ ተመለሰ፤ ንጉሡም ልብናን ሲወጋ አገኘው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የአሦራውያን ባለ ሥልጣን ንጉሡ ላኪሸን ለቆ በአቅራቢያ ወዳለችው ወደ ሊብና ከተማ በመሄድ እዚያ በመዋጋት ላይ መሆኑን ሰማ፤ ስለዚህ ወደዚያ ሄደ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ከለ​ኪሶ እንደ ራቀ ሰምቶ ነበ​ርና ራፋ​ስ​ቂስ ተመ​ልሶ በል​ብና ሲዋጋ አገ​ኘው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የአሦርም ንጉሥ ከለኪሶ እንደ ራቀ ሰምቶ ነበርና ራፋስቂስ ተመልሶ በልብና ሲዋጋ አገኘው።

Ver Capítulo



ኢሳይያስ 37:8
10 Referencias Cruzadas  

ከዚያም ጊዜ ጀምሮ ኤዶም ከይሁዳ ተገዢነት ነጻ ወጣች፤ በዚያኑ ጊዜም የልብና ከተማ ዐመፀች።


ኤዶምያስ ግን በይሁዳ ላይ እስከ ዛሬ ድረስ ዓመፀ፥ በዚያንም ዘመን ልብና ደግሞ በእርሱ ላይ ዓመፀ፥ የአባቶቹን አምላክ ጌታን ትቶ ነበርና።


ሴዴቅያስ መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሀያ አንድ ዓመት ጎልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ የእናቱም ስም አሚጣል ይባል ነበር፥ እርሷም የሊብና ሰው የሆነው የኤርምያስ ልጅ ነበረች።


ኢያሱም ከእርሱም ጋር እስራኤል ሁሉ ከመቄዳ ወደ ልብና አለፉ፥ ልብናንም ወጉ።


የየርሙት ንጉሥ፥ የለኪሶ ንጉሥ፥


ለኪሶ፥ ቦጽቃት፥ ዔግሎም፥


ለካህኑም ለአሮን ልጆች እነዚህን ሰጡ፤ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን ኬብሮንና መሰማሪያዋን፥ ልብናንና መሰማሪያዋን፥