ኢሳይያስ 36:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባዶ ቃል የጦር ስልትና ኃይል የሚሆንህ ይመስልህል? አሁንም በእኔ ላይ ያመፅኸው በማን ተማምነህ ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጦር ስልትና ኀይል አለኝ ትላለህ፤ ነገር ግን ባዶ ቃል ብቻ ትናገራለህ። በእኔ ላይ ያመፅኸው በማን ተደግፈህ ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከንቱ ቃላት የጦርነት ስልትና ኀይል ይሆናል ብለህ ታስባለህን? ኧረ ለመሆኑ በእኔ ላይ ያመፅከው በማን ተማምነህ ነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምክርና በከንፈር ንግግር ጦርነት ይሆናልን? አሁንም በእኔ ላይ ያመፅኸው በማን ተማምነህ ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ፦ ለሰልፍ የሆነው ምክርህና ኃይልህ ከንቱ ነገር ነው አልሁ፥ አሁንም በእኔ ላይ ያመፅኸው በማን ተማምነህ ነው? |
ስለዚህም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ሆኖ ስለሚረዳው የሚሠራው ሁሉ በተቃና ሁኔታ ይከናወንለት ነበር፤ ሕዝቅያስ በአሦር ንጉሠ ነገሥት ላይ ዐምፆ ለእርሱ መገዛትን አሻፈረኝ አለ።
በእርግጥ ከጌታ ቁጣ የተነሣ ከፊቱ አውጥቶ እስኪጥላቸው ድረስ ይህ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላይ ሆነ፤ ሴዴቅያስም በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ።
ነገር ግን በእርሱ ላይ ዐመጸ፥ ፈረሶችንና ብዙ ሕዝብም እንዲሰጡት መልእክተኞቹን ወደ ግብጽ ላከ። ይሳካለታልን? እነዚህን ነገሮች ያደረገስ ያመልጣልን? ቃል ኪዳንን አፍርሶስ ያመልጣልን?