ኢሳይያስ 34:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ጉጉት ጎጆ ሠርታ እንቁላልን ትጥላለች፥ ትቀፈቅፋለችም፤ ጫጩቶቿንም በክንፏ ትሰበስባለች፤ በዚያም ደግሞ አሞራዎች ጥንድ ጥንድ ሆነው ይሰበሰባሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጕጕት በዚያ ጐጆ ሠርታ ዕንቍላል ትጥላለች፤ ትቀፈቅፋለች፤ ጫጩቶቿን በክንፎቿ ትታቀፋቸዋለች፤ ጭላቶችም ጥንድ ጥንድ ሆነው፣ ለርቢ በዚያ ይሰበሰባሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም ጒጒቶች ጎጆ ሠርተው እንቊላል ይጥላሉ፤ እንቁላሎቻቸውንም ፈልፍለው በክንፎቻቸው ጥላ ሥር ይንከባከባሉ፤ አሞራዎችም ከጓደኞቻቸው ጋር በዚያ ይሰባሰባሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያ ጃርቶች ይዋለዳሉ፤ ምድርም ልጆችዋን በኀይል ታድናለች፤ ዋሊያዎች በዚያ ይገናኛሉ፤ ፊት ለፊትም ይተያያሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ዋሊያ ቤትዋን ትሠራለች እንቍላልን ትጥላለች ትቀፈቅፈውማለች ልጆችዋንም በጥላዋ ትሰበስባለች፥ በዚያም ደግሞ አሞራዎች እያንዳንዳቸው ከባልንጀሮቻቸው ጋር ይሰበሰባሉ። |