ኢሳይያስ 33:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሕዛብም እንደ ተቃጠለ ኖራ፥ ተቆርጦም በእሳት እንደ ተቃጠለ እሾህ ይሆናሉ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቦች ኖራ እንደሚወጣው ድንጋይ ይቃጠላሉ፤ እንደ እሾኽ ቍጥቋጦ በእሳት ይጋያሉ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ለኖራ እንደሚቃጠሉና ለእሳት እንደሚቈረጥ እሾኽ ትሆናላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሕዛብም በእርሻ ውስጥ ተቈርጦ እንደ ተጣለና በእሳት እንደ ተቃጠለ እሾህ የተቃጠሉ ይሆናሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሕዛብም እንደ ተቃጠለ ኖራ፥ ተቆርጦም በእሳት እንደ ተቃጠለ እሾህ ይሆናሉ። |
እንግዲህ ርኩሰት እንደ እሳት ይቀጣጠላል፤ እሾህንና ኩርንችትን ይበላል፤ ጥቅጥቅ ያለውን ደን ያነዳል፤ ጢሱም ተትጐልጉሎ እንደ ዐምድ ይቆማል።
ጌታ እንዲህ ይላል፦ “የኤዶምያስን ንጉሥ ዐፅም አመድ እስኪሆን ድረስ አቃጥሎአልና ስለ ሦስት የሞዓብ ኃጢአት ስለ አራትም መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም።