ኢሳይያስ 33:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አሁን እነሣለሁ” ይላል ጌታ፥ “አሁን እከበራለሁ፤ አሁን ከፍ ከፍ እላለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “አሁን እነሣለሁ፤ አሁን ከፍ ከፍ እላለሁ፤ አሁን እከብራለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “አሁን እኔ እነሣለሁ፤ እከበራለሁ፤ ከፍ ከፍም እላለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “አሁን እነሣለሁ፤ አሁን እከብራለሁ፤ አሁን ከፍ ከፍ እላለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁን እነሣለሁ ይላል እግዚአብሔር፥ አሁን እከበራለሁ፥ አሁን ከፍ ከፍ እላለሁ። |
ስለዚህ ጌታ፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ በፈረጠሙ ጦረኞቹ ላይ የሚያከሳ በሽታ ይልካል፤ ከክብሩም በታች እንደ ነበልባል የሚንቦገቦግ እሳት ይለኰሳል።
ጌታ ምድርን ለማናወጥ በሚነሣበት ጊዜ፤ ሰዎች ከአስፈሪነቱ እንዲሁም ከግርማው የተነሣ፤ ወደ ድንጋይ ዋሻ፤ ወደ ዐለት ስንጣቂ ሮጠው ይገባሉ።
ስለዚህ “ጠብቁኝ” ይላል ጌታ፤ ለመበዝበዝ እስከምነሣበት ቀን ድረስ፥ ፍርዴ ሕዝቦችን ለመሰብሰብ፥ መንግሥታትንም ለማከማቸት ነው፥ ይህም መዓቴንና የቁጣዬን ትኩሳት ሁሉ ለማፍሰስ ነው፤ በቅንዓቴ እሳት ምድርም ሁሉ ትበላለችና።