La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢሳይያስ 32:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጥንቃቄ የሌላቸው ሰዎች ልብ እውቀትን ታስተውላለች፤ የተብታቦችም ምላስ ተፍታታና ደኅና አድርጋ ትናገራለች።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የችኵል አእምሮ ያውቃል፤ ያስተውላልም፤ የተብታባም ምላስ የተፈታ ይሆናል፤ አጥርቶም ይናገራል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ችኲሎች የነበሩ በትዕግሥት የሚያመዛዝኑ ይሆናሉ፤ ተብታባ አንደበት የነበራቸው አንደበተ ርቱዖች ይሆናሉ፤ ንግግራቸውም ግልጥ ይሆናል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የደ​ካ​ሞች ሰዎች ልብ ዕው​ቀ​ትን ትሰ​ማ​ለች፤ የተ​ብ​ታ​ቦ​ችም ምላስ ፈጥና የሰ​ላ​ምን ነገር ትማ​ራ​ለች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ጥንቃቄ የሌላቸው ሰዎች ልብ እውቀትን ታስተውላለች፥ የተብታቦችም ምላስ ደኅና አድርጋ ትናገራለች።

Ver Capítulo



ኢሳይያስ 32:4
14 Referencias Cruzadas  

ጌታም እንዲህ አለው፦ “የሰውን አፍ የፈጠረ ማን ነው? ዲዳ ወይም ደንቆሮ ወይም የሚያይ ወይም ዕውር ያደረገ ማን ነው? እኔ ጌታ አይደለሁምን?


አፍሽ ለወዳጄ እየጣፈጠ እንደሚገባ፥ የተኙትን ከንፈሮች ይናገሩ ዘንድ እንደሚያደርግ፥ እንደ ማለፊያ የወይን ጠጅ ነው።


በመንፈስም የሳቱ ወደ ማስተዋል ይደርሳሉ፤ የሚያጉረመርሙም ምክርን ይቀበላሉ።


ፈሪ ልብ ላላቸው፦ “እነሆ፥ አምላካችሁ ለበቀል፥ ብድራት ለመመለስ ይመጣል፤ መጥቶም ያድናችኋልና በርቱ፥ አትፍሩ!” በሉአቸው።


በዚያን ጊዜም የዕውሮች ዐይን ይበራል፤ የደንቆሮችም ጆሮ ይከፈታል።


በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ “የሰማያትና የምድር ጌታ አባት ሆይ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ።


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ! የተባረክህ ነህ! በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና።


ጴጥሮስና ዮሐንስም በግልጥ እንደ ተናገሩ ባዩ ጊዜ፥ መጽሐፍን የማያውቁና ያልተማሩ ሰዎች እንደ ሆኑ አስተውለው አደነቁ፤ ከኢየሱስም ጋር እንደ ነበሩ አወቁአቸው፤


የእግዚአብሔርም ቃል እየሰፋ ሄደ፤ በኢየሩሳሌምም የደቀ መዛሙርት ቍጥር እጅግ እየበዛ ሄደ፤ ከካህናትም ብዙ ሰዎች ለሃይማኖት የታዘዙ ሆኑ።


ነገር ግን “ቀድሞ እኛን ያሳድድ የነበረው፥ እርሱ በፊት ያጠፋው የነበረውን እምነት አሁን ይሰብካል” ተብሎ ሲነገር ይሰሙ ነበር፤