ኢሳይያስ 23:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጥንት ዘመን ተቆርቁራ የነበረችው፥ እሩቅ ምድር ድረስ እድትሰፍር እግሮችዋ ያጓጓዟት፥ የደስታችሁ ከተማ ይህች ናት? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግሮቿ ሩቅ አገር የወሰዷት፣ በዚያም እንድትሰፍር ያደረጓት፣ ጥንታዊቷ የድሮ ከተማ፣ የተድላ ከተማችሁ ይህች ናትን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቦችዋ ወደ ሩቅ አገር ሄደው ለመስፈር የቻሉት ለዘመናት ተደስታ ትኖር የነበረችው ከተማ እንዲህ ሆና ቀረችን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተማርካችሁ ሂዱ እንጂ ይህች ዕረፍት የእናንተ አይደለችም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቀድሞ ዘመን ተመሥርታ የነበረችው፥ በዚያም እንደ እንግዳ ሆና ትኖር ዘንድ እግሮችዋ ወደ ሩቅ ያፈለሱአት የደስታችሁ ከተማ ይህች ናትን? |
አንቺ ጩኸትና ፍጅት የሞላብሽ ከተማ፥ የፈንጠዚያ ከተማ ሆይ፥ በአንቺ ውስጥ የተገደሉት በሰይፍ የተገደሉ አይደሉምን፥ በሰልፍስ የሞቱ አይደሉም?