ኢሳይያስ 19:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሸማኔዎችዋም ሁሉ ቅስማቸው ይሰበራል፥ የደመወዘኞችም ልብ ይሰበራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልብስ ሠሪዎች ያዝናሉ፤ ደመወዝተኞችም ልባቸው ይሰበራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሸማኔዎች ግራ ይጋባሉ፤ ደመወዝተኞችም እየጮኹ ያለቅሳሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእነርሱም የሚሠሩ ይሠቃያሉ፤ በሐር ኩብ የሚነግዱ ሁሉ ይቀልጣሉ፤ ልቡናቸውም ያዝናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደገፋዎችዋም ሁሉ ይሰባበራሉ፥ የደመወዘኞችም ነፍስ ትተክዛለች። |
ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አሮንን እንዲህ በለው፦ ‘በትርህን ውሰድ፥ በግብጽ ውኆች፥ በፈሳሾቻቸው፥ በወንዞቻቸው፥ በኩሬዎቻቸው፥ በውኃ ማጠራቀሚያዎቻቸውም ላይ ደም እንዲሆኑ እጅህን ዘርጋ፤ በግብጽም ምድር ሁሉ በእንጨት ዕቃና በድንጋይ ዕቃ ሁሉ ደም ይሆናል።’”
ሙሴም ፈርዖንን፦ “እንቁራሪቶቹ ከአንተና ከቤቶችህ እንዲጠፋ፥ በዓባይ ወንዝም ብቻ እንዲቀሩ፥ ለአንተ፥ ለአገልጋዮችህና ለሕዝብህ መቼ እንድጸልይ ንገረኝ” አለው።