ኢሳይያስ 14:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምድር ሁሉ ላይ እግዚአብሔር ያሰበው አሳብ ይህ ነው፥ በአሕዛብም ሁሉ ላይ የተዘረጋች እጅ ይህች ናት።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለምድር ሁሉ የታሰበው ዕቅድ ይህ ነው፤ በአሕዛብም ሁሉ ላይ የተዘረጋው እጅ ይኸው ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መላውን ዓለም በሚመለከት ያለኝም ዕቅድ ይህ ነው፤ መንግሥታትን ለመቅጣት ክንዴን ዘርግቼአለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምድር ሁሉ ላይ እግዚአብሔር ያሰበው ዐሳብ ይህ ነው፤ በአሕዛብም ሁሉ የተዘረጋች እጅ ይህች ናት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምድር ሁሉ ላይ እግዚአብሔር ያሰበው አሳብ ይህ ነው፥ በአሕዛብም ሁሉ ላይ የተዘረጋች እጅ ይህች ናት። |
የጌታ ቁጣ በሕዝቡ ላይ ነዶአል፤ እጁን አንሥቶ መቶአቸዋል፤ ተራሮች ራዱ፤ ሬሳዎችም በመንገድ ላይ እንደ ተጣለ ጥራጊ ሆኑ፤ ይህ ሁሉ ሆኖ ግን ቁጣው ገና አልተመለሰም፤ እጁም እንደ ተነሣ ነው።