ሆሴዕ 13:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም እኔ እንደ አንበሳ እሆንባቸዋለሁ፥ እንደ ነብርም በመንገድ አጠገብ አደባባቸዋለሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እንደ አንበሳ እመጣባቸዋለሁ፤ እንደ ነብርም በመንገድ አደባባቸዋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ የተነሣ እንደ አንበሳና በመንገድ እንደሚያደባ ነብርም እሆንባችኋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም ለይሁዳ ቤት እንደ አንበሳ፥ ለኤፍሬምም እንደ ነብር ሆንሁባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህም እኔ እንደ አንበሳ ሆንሁባቸው፥ እንደ ነብርም በመንገድ አጠገብ አደባባቸዋለሁ፥ |
ስለዚህ ኃጢአታቸው በዝቶአልና፥ የከዳተኝነታቸውም ብዛት ጸንቶአልና ስለዚህ አንበሳ ከዱር ወጥቶ ይሰብራቸዋል፥ የበረሀም ተኩላ ያጠፋቸዋል፥ ነብርም በከተሞቻቸው ላይ ነቅቶ ይጠብቃል፥ ከዚያም የሚወጣ ሁሉ ይነጠቃል።
እኔም ለኤፍሬም እንደ አንበሳ፥ ለይሁዳም ቤት እንደ አንበሳ ደቦል እሆናለሁና፤ እኔ ራሴ ነጥቄ እሄዳለሁ እወስዳለሁም፥ ሊያድንም የሚችል ማንም የለም።
እንዲህም አለ፦ “ጌታ በጽዮን ሆኖ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮኻል፥ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ድምፁን ያስተጋባል፤ የእረኞችም ማሰማርያዎች ይጠወልጋሉ፥ የቀርሜሎስም ራስ ይደርቃል።”
ያየሁትም አውሬ ነብር ይመስል ነበር፤ እግሮቹም እንደ ድብ እግሮች፥ አፉም እንደ አንበሳ አፍ ነበሩ። ዘንዶውም ኀይሉን፥ ዙፋኑንና ትልቅ ሥልጣንን ሰጠው።