ሆሴዕ 13:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቁጣዬ ንጉሥን ሰጠሁህ፥ በመዓቴም ሻርሁት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በቍጣዬ ንጉሥን ሰጠሁህ፤ በመዓቴም ሻርሁት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቊጣዬ ነገሥታትን ሰጥቻችሁ ነበር፤ ነገር ግን በከፍተኛ ቊጣዬ አጠፋኋቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቍጣዬ ንጉሥን ሰጠሁህ፤ በመዓቴም ሻርሁት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቁጣዬ ንጉሥን ሰጠሁህ፥ በመዓቴም ሻርሁት። |
ለራሳቸው ነገሥታትን አነገሡ፥ ከእኔም ዘንድ አይደለም፤ አለቆችንም ሾሙ፥ እኔም አላወቅሁም፤ ለመጥፊያቸው ከብራቸውና ከወርቃቸው ጣዖታትን ለራሳቸው ሠሩ።
ዛሬ ግን ከመከራችሁና ከጭንቃችሁ ሁሉ የሚያድናችሁን አምላካችሁን ንቃችሁ፤ ‘የለም፤ ንጉሥ አንግሥልን’ አላችሁ። ስለዚህ በየነገዳችሁና በየወገናችሁ ሆናችሁ በጌታ ፊት ቅረቡ።”
ጌታ ሳሙኤልን፥ “በእስራኤል ላይ እንዳይነግሥ ለናቅሁት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው? ወደ ቤተልሔሙ ሰው ወደ እሴይ ስለምልክህ፥ ዘይት በቀንድ ሞልተህ ሂድ፤ ከልጆቹ አንዱ ንጉሥ ይሆን ዘንድ መርጬዋለሁ” አለው።