ዕብራውያን 6:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እሾህና ኩርንችትን ግን ብታወጣ፥ ጥቅም አይኖራትም፤ ለመረገምም ትቀርባለች፤ መጨረሻዋም መቃጠል ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን እሾኽና አሜከላ የምታበቅል መሬት ዋጋ ቢስ ትሆናለች፤ መረገሚያዋም ተቃርቧል፤ መጨረሻዋም በእሳት መቃጠል ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እሾኽና አሜከላ ብታበቅል ግን ዋጋቢስ ትሆናለች፤ በቅርብ ጊዜም ትረገማለች፤ መጨረሻዋም በእሳት መቃጠል ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እሾህንና ኵርንችትን ብታወጣ ግን የተጣለች ናት፤ ለመርገምም የቀረበች ናት፤ ፍጻሜዋም ለመቃጠል ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እሾህና ኵርንችትን ግን ብታወጣ፥ የተጣለች ናት ለመረገምም ትቀርባለች፥ መጨረሻዋም መቃጠል ነው። |
እርሱ በምድረ በዳ እንዳለ ቁጥቋጦ ነው፥ መልካምም በመጣ ጊዜ አያይም፤ ሰውም በማይቀመጥበት፥ ጨው ባለበት ምድር፥ በምድረ በዳ በደርቅ ስፍራ ይቀመጣል።
ጌታም ከእንግዲህ ወዲህ የሥራችሁን ክፋትና ያደረጋችሁትን ርኩሰት መታገሥ አልቻለም፤ ስለዚህ ምድራችሁ ባድማ መሣቀቂያም መረገሚያም ሆናለች ዛሬም እንደሆነ የሚኖርባት የለም።
ለደቡብም ዱር፦ የጌታን ቃል ስማ፤ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በአንተ ውስጥ እሳት አነድዳለሁ፤ በውስጥህም ያለውን የለመለመውንና የደረቀውን ዛፍ ሁሉ ይበላል፤ የሚቃጠል ነበልባል አይጠፋም፤ ከደቡብም ጀምሮ እስከ ሰሜን ድረስ ፊት ሁሉ ይቃጠልበታል።
“እነሆ፥ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድ ቀን ይመጣል፤ ትዕቢተኞች ሁሉና ኃጢአትን የሚሠሩ ሁሉ ገለባ ይሆናሉ፤ የሚመጣውም ቀን ያቃጥላቸዋል” ይላል የሠራዊት ጌታ፤ ሥርንና ቅርንጫፍንም አያስቀርላቸውም።
ከዚህ በኋላ በግራው ያሉትን ደግሞ እንዲህ ይላቸዋል ‘እናንተ የተረገማችሁ! ከእኔ ወዲያ ራቁ! ለዲያብሎስና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀው ወደ ዘለዓለም እሳት ሂዱ።