ዕብራውያን 3:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ ባለማመናቸው ጠንቅ ሊገቡ እንዳልተቻላቸው እናያለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ ሊገቡ ያልቻሉት ካለማመናቸው የተነሣ እንደ ሆነ እንረዳለን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ ሊገቡ ያልቻሉት ባለማመናቸው ምክንያት መሆኑን እናያለን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አላመኑምና፥ ለመግባት እንዳልቻሉ እነሆ፥ እናያለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባለማመናቸውም ጠንቅ ሊገቡ እንዳልተቻላቸው እናያለን። |
በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን በራሱ ምስክር አለው፤ እግዚአብሔርን የማያምን ግን እግዚአብሔር ስለ ልጁ የመሰከረውን ምስክርነት ስላላመነ ሐሰተኛ አድርጎታል።
ነገር ግን ሁሉን ነገር አንድ ጊዜ ያወቃችሁትን እናንተን፥ ጌታ ከግብጽ አገር ሕዝቡን አድኖ የማያምኑትን በኋላ እንዳጠፋቸው ላሳስባችሁ እወዳለሁ።