ዕብራውያን 3:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአርባ ዓመታት፤ ስለዚህ ያን ትውልድ ተቆጥቼ “ዘወትር በልባቸው ይስታሉ፤ መንገዴን ግን አላወቁም፤” አልኩ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያም ትውልድ ላይ የተቈጣሁት ለዚህ ነበር፤ እንዲህም አልሁ፤ ‘በልባቸው ዘወትር ይስታሉ፤ መንገዴንም አላወቁም።’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ስለዚህ ያንን ትውልድ ተቈጥቼ፥ ‘ልባቸው ዘወትር ይሳሳታል፤ መንገዴንም አላወቁም’ አልኩ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ ይህቺን ትውልድ ተቈጣኋት፤ እንዲህም አልሁ፦ ‘ልባቸው ዘወትር ይስታል፤ እነርሱ ግን መንገዴን አላወቁም።’ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ያን ትውልድ ተቆጥቼ፦ ዘወትር በልባቸው ይስታሉ መንገዴን ግን አላወቁም አልሁ፤ |
እነዚህ ደግሞ ከወይን ጠጅ የተነሣ ይስታሉ፤ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይንገዳገዳሉ፤ ካህኑና ነቢዩ ከሚያሰክር መጠጥ የተነሣ ይስታሉ፥ በወይን ጠጅም ይቀባዥራሉ፥ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይንገዳገዳሉ፤ ራእይ ሲያዩ ይስታሉ፥ በፍርድም ይሰናከላሉ።
“ሕዝቤ ሰንፈዋልና አላወቁኝም፤ ሰነፎች ልጆች ናቸው፥ ማስተዋልም የላቸውም፤ ክፉ ነገርን ለማድረግ ብልሃተኞች ናቸው፥ በጎ ነገርን ማድረግ ግን አያውቁም።”