ዕብራውያን 2:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአብርሃምን ዘር ለመርዳት እንጂ ትኩረቱ ለመላእክት አይደለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ የመጣው መላእክትን ለመርዳት ሳይሆን፣ የአብርሃምን ዘር ለመርዳት እንደ ሆነ ግልጽ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኢየሱስ ፍላጎት መላእክትን ሳይሆን የአብርሃምን ዘር ለመርዳት ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የነሣውን ከአብርሃም ዘር እንጂ ከመላእክት የነሣው አይደለምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአብርሃምን ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም። |
የተስፋውም ቃል የተነገረው ለአብርሃምና ለዘሩ ነበር። ለብዙዎች እንደሆነ “ለዘሮችህ” አይልም፤ ነገር ግን ለአንድ እንደሆነ “ለዘርህም” ይላል፤ እርሱም ክርስቶስ ነው።
ስለዚህ የሕዝብን ኃጢአት ለማስተስረይ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ የሚምርና የታመነ ሊቀ ካህናት እንዲሆን፥ በነገር ሁሉ ወንድሞቹን ሊመስል ተገባው።