ዕንባቆም 3:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ሆይ ንዴትህ በወንዞች ላይ ነውን? ወይስ ቁጣህ በወንዞች ላይ ወይም መዓትህ በባሕር ላይ ነውን? በፈረሶችህ፥ በማዳን ሰረገሎች ላይ ተቀምጠሃልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ በወንዞች ላይ ተቈጣህን? መዓትህስ በምንጮች ላይ ነበርን? በፈረሶችህና በድል አድራጊ ሠረገሎችህ በጋለብህ ጊዜ፣ በባሕር ላይ ተቈጥተህ ነበርን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! ፈረሶችህንና ሠረገላዎችህን ወደ ድል በመራኸቸው ጊዜ፥ ኀይለኛው ቊጣህ በወንዞች ላይ ነበርን? ወይስ በባሕሩ ላይ ተቈጥተህ ነበርን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውኑ እግዚአብሔር በወንዞች ላይ ተቈጥቶአልን? ቍጣህ በወንዞች ላይ፥ መዓትህም በባሕር ላይ ነውን? በፈረሶችህና በማዳንህ ሰረገሎች ላይ ተቀምጠሃልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ እግዚአብሔር በወንዞች ላይ ተቈጥቶአልን? ቍጣህ በወንዞች ላይ፥ መዓትህም በባሕር ላይ ነውን? በፈረሶችህና በማዳንህ ሰረገሎች ላይ ተቀምጠሃልና። |
ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አሮንን እንዲህ በለው፦ ‘በትርህን ውሰድ፥ በግብጽ ውኆች፥ በፈሳሾቻቸው፥ በወንዞቻቸው፥ በኩሬዎቻቸው፥ በውኃ ማጠራቀሚያዎቻቸውም ላይ ደም እንዲሆኑ እጅህን ዘርጋ፤ በግብጽም ምድር ሁሉ በእንጨት ዕቃና በድንጋይ ዕቃ ሁሉ ደም ይሆናል።’”
ሙሴና አሮንም ልክ ጌታ እንዳዘዛቸው እንዲሁ አደረጉ፤ በትሩንም አነሣ፥ በፈርዖንና በአገልጋዮቹም ፊት በዓባይ ወንዝ የነበረውን ውኃ መታ፤ በዓባይ ወንዝ ላይ የነበረው ውኃ ሁሉ ወደ ደም ተቀየረ።
ስለ ግብጽ የተነገረ ትንቢት። እነሆ፥ ጌታ በፈጣን ደመና እየበረረ ወደ ግብጽ ይመጣል፤ የግብጽም ጣዖታት በፊቱ ይርዳሉ፤ የግብጽም ልብ በውስጥዋ ይቀልጣል።
በመጣሁስ ጊዜ ሰው ስለምን አልነበረም? በጠራሁስ ጊዜ የሚመልስ ስለምን አልነበረም? መታደግ እንዳትችል እጄ አጭር ሆናለችን? ወይስ ለማዳን ኃይል የለኝም? እነሆ፥ በገሠጽሁ ጊዜ ባሕርን አደርቃለሁ፥ ወንዞችንም ምድረ በዳ አደርጋቸዋለሁ፤ ውኃም አጥተው ዓሦቻቸው ይገማሉ፥ በጥማትም ይሞታሉ።
ስድስተኛውም መልአክ ጽዋውን በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ ላይ አፈሰሰ፤ ከፀሐይም መውጫ ለሚመጡ ነገሥታት መንገድ እንዲሰናዳላቸው ውሃው ደረቀ።