La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዕንባቆም 2:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታም መለሰልኝ፥ እንዲህም አለ፦ ራእዩን ጻፍ፤ የሚያነበው እንዲሮጥ በጽላት ላይ በግልፅ አድርገው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “አንባቢው እንዲፈጥን፣ ራእዩን ግልጽ አድርገህ በጽላት ላይ ጻፍ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰልኝ፦ “የምገልጥልህን ራእይ ጻፍ፤ በቀላሉ እንዲነበብም አድርገህ በሰሌዳ ላይ ቅረጸው፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግዚአብሔርም መለሰልኝ እንዲህም አለ፦ አንባቢው ይፈጥን ዘንድ ራእዩን ጻፍ፥ በጽላትም ላይ ግለጠው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔርም መለሰልኝ እንዲህም አለ፦ አንባቢው ይፈጥን ዘንድ ራእዩን ጻፍ፥ በጽላትም ላይ ግለጠው።

Ver Capítulo



ዕንባቆም 2:2
18 Referencias Cruzadas  

አሁንም ሂድ፥ ለሚመጣውም ዘመን ለዘለዓለም እንዲሆን በሰሌዳ ላይ በመጽሐፍም ውስጥ ጻፍላቸው።


ጌታም እንዲህ አለኝ፦ “ትልቅ ሰሌዳ ወስደህ፤ ‘ማኸር-ሻላል-ሃሽ-ባዝ’ ብለህ በተለመደው በሰው ፊደል ጻፍበት።


“የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ የነገርሁህን ቃላት ሁሉ በመጽሐፍ ጻፍ።


በመጽናትና መጻሕፍት በሚሰጡት መጽናናት ተስፋ ይሆንልን ዘንድ አስቀድሞ የተጻፈው ነገሮች ሁሉ ለትምህርታችን ተጽፎአል።


ነገር ግን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሌሎችን ለማስተማር፥ ዐሥር ሺህ ቃላት በልሳን ከምናገር ይልቅ፥ አምስት ቃላት በአእምሮዬ ብናገር ይሻላል።


እንግዲህ እንዲህ ያለ ተስፋ ካለን፥ አብዝተን በድፍረት እንናገራለን፤


የዚህንም ሕግ ቃሎች ሁሉ ግልጽ አድርገህ በድንጋዮቹ ላይ ጻፍ።”


“እንግዲህ ይህን መዝሙር ለራሳችሁ ጻፉ፤ ለእስራኤል ልጆችም አስተምሩ፤ ስለ እኔ ምስክር ይሆንባቸው ዘንድ እንዲዘምሩ አድርጉ።


ስለዚህም ሙሴ ይህን መዝሙር በዚያች ቀን ጻፈ፤ ለእስራኤላውያንም አስተማራቸው።


ከሰማይም እንዲህ የሚል ድምፅ ሰማሁ። “ይህንን ጻፍ፥ ከእንግዲህ ወዲህ በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብፁዓን ናቸው።” መንፈስም “አዎን! ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ፥ ሥራቸው ይከተላቸዋልና፤” ይላል።


መልአኩም “ወደ በጉ ሰርግ እራት የተጠሩ ብፁዓን ናቸው፤” ብለህ ጻፍ፤ አለኝ። ደግሞም “ይህ የእግዚአብሔር እውነተኛ ቃል ነው፤” አለኝ።