La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 9:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንዲህም አለ፦ “ከነዓን የተረገመ ይሁን! ለወንድሞቹም የባርያዎች ባርያ ይሁን።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንዲህም አለ፤ “ከነዓን የተረገመ ይሁን፤ ለወንድሞቹም፣ የባሪያ ባሪያ ይሁን።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እንዲህም አለ፤ “ከነዓን የተረገመ ይሁን! ለወንድሞቹ የአገልጋዮች አገልጋይ ይሁን፤ እንደገናም እንዲህ አለ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ኖኅም እን​ዲህ አለ፥ “ከነ​ዓን ርጉም ይሁን፤ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም የባ​ሪ​ያ​ዎች ባሪያ ይሁን።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እንዲህም አለ፥ ከነዓን ርጉም ይሁን ለወንድሞቹም የባሪያዎች ባሪያ ይሁን።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 9:25
15 Referencias Cruzadas  

ጌታ እግዚአብሔርም እባቡን አለው፦ “ይህን በማድረግህ፥ ከእንስሳት ከምድር አራዊትም ሁሉ ተለይተህ አንተ የተረገምህ ትሆናለህ፤ በሆድህም ትሄዳለህ፥ በሕይወትህም ዘመን ሁሉ አፈርን ትበላለህ።


አሁንም የወንድምህን ደም ከእጅህ ለመቀበል አፍዋን በከፈተች በምድር ላይ አንተ የተረገምህ ነህ።


ቁጣቸው ርጉም ይሁን፥ ጽኑ ነበርና፥ ኩርፍታቸውም፥ ብርቱ ነበርና፥ በያዕቆብ እከፋፍላቸዋለሁ፥ በእስራኤልም እበታትናቸዋለሁ።


ከመርከቡ የወጡት የኖኅ ልጆች ሴም፥ ካምና ያፌት ናቸው፤ ካም የከነዓን አባት ነው።


የከነዓን አባት፥ ካምም፥ የአባቱን ዕራቁቱን መሆን አየ፥ ወደ ውጭም ወጥቶ ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው።


ኖኅም ከወይን ጠጁ ስካር ሲነቃ፥ ታናሽ ልጁ ያደረገበትን አወቀ።


ከዚህ በኋላ በግራው ያሉትን ደግሞ እንዲህ ይላቸዋል ‘እናንተ የተረገማችሁ! ከእኔ ወዲያ ራቁ! ለዲያብሎስና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀው ወደ ዘለዓለም እሳት ሂዱ።


ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ኃጢአት የሚያደርግ ሁሉ የኃጢአት ባርያ ነው።


“‘አባቱን ወይም እናቱን የሚያቃልል የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል።


“የሆድህ ፍሬ፥ የምድርህም ፍሬ፥ የከብትህ መንጋ፥ የበግና የፍየል መንጋ ይረገማሉ።


እንግዲህ አሁን የተረገማችሁ ናችሁ፤ እናንተም ለአምላኬ ቤት እንጨት ቈራጭ ውኃም ቀጂ ባርያዎች ለዘለዓለም ትሆናላችሁ።”


በዚያም ቀን ኢያሱ በመረጠው ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ ለማኅበሩና ለጌታ መሠዊያ እንጨት ቈራጮች ውኃም ቀጂዎች አደረጋቸው።