ዘፍጥረት 9:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኖኅ ቀዳሚ ገበሬ ነበረ፤ የወይን ተክልንም ተከለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኖኅ ገበሬ ነበረና ወይን ተከለ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኖኅ ገበሬ ነበረ፤ የወይን ተክልንም መትከል ጀመረ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኖኅም ገበሬ መሆን ጀመረ፤ ወይንም ተከለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኖኅም ገበሬ መሆን ጀመረ፥ ወይንም ተከለ። |
ፀሐይ መልኬን አክስሎታልና ጥቁር ስለ ሆንኩ አትዩኝ፥ የእናቴ ልጆች ተጣሉኝ፥ የወይን ቦታዎችንም ጠባቂ አደረጉኝ፥ ነገር ግን የእኔን ወይን ቦታ አልጠበቅሁም።
ከቶ በገዛ ገንዘቡ በወታደርነት የሚያገለግል ማን ነው? ወይን ተክሎ ፍሬውን የማይበላ ማን ነው? ወይስ መንጋ እየጠበቀ ከመንጋው ወተት የማይጠጣ ማን ነው?