እግዚአብሔር ኖኅንና ከእርሱ ጋር በመርከቡ ውስጥ የነበሩትን አራዊትና እንስሶች ሁሉ አሰበ። ነፋስ በምድር ላይ እንዲነፍስ አደረገ፥ ውኃውም ጎደለ፥
ዘፍጥረት 9:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም ከእናንተ ጋር ላሉትም ሕያው ነፍስ ላላቸው ሁሉ፥ ከእናንተ ጋር ከመርከብ ለወጡት አእዋፍ፥ ለእንስሳትም፥ ለምድር አራዊትም ሁሉ፥ ለየትኛውም የምድር አራዊት ሁሉ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ከእናንተ ጋራ ከነበሩት ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ፦ ከወፎች፣ ከቤት እንስሳት፣ ከዱር እንስሳት፣ ከእናንተ ጋራ ከመርከቧ ከወጡት በምድር ላይ ካሉት ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ጋራ ኪዳን እገባለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ሕይወት ካላቸው ፍጥረቶች ሁሉ፥ ማለትም ከወፎች፥ ከእንስሶችና ከአራዊት፥ ከአንተ ጋር ከመርከቡ ውስጥ ከወጡት ፍጥረቶችና ዘሮቻቸው ሁሉ ጋር ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእናንተ ጋር ላሉትም፥ ሕያው ነፍስ ላላቸው ሁሉ፥ ከእናንተ ጋር ከመርከብ ለወጡት ለወፎች፥ ለእንስሳትም፥ ለምድር አራዊትም ሁሉ፥ ለማንኛውም ለምድር አራዊት ሁሉ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእናንተ ጋር ከመርከብ ለወጡት ለወፎች፥ ለእንስሳትም ለምድር አራዊትም ሁሉ ለማንኛውም ለምድር አራዊት ሁሉ ይሆናል። |
እግዚአብሔር ኖኅንና ከእርሱ ጋር በመርከቡ ውስጥ የነበሩትን አራዊትና እንስሶች ሁሉ አሰበ። ነፋስ በምድር ላይ እንዲነፍስ አደረገ፥ ውኃውም ጎደለ፥
ቃል ኪዳኔንም ለእናንተ እመሰርታለሁ፥ ሕያው ፍጥረት ሁሉ ዳግመኛ በጥፋት ውኃ አይጠፉም፥ ምድርንም ለማጥፋት ዳግመኛ የጥፋት ውኃ አይመጣም።”
በዚያም ቀን ከምድር አራዊትና ከሰማይ ወፎች በምድርም ላይ ከሚሳቡ ፍጥረቶች ጋር ቃል ኪዳን አደርግላቸዋለሁ፤ ቀስትንና ሰይፍን ጦርነትንም ከምድሪቱ አስወግዳለሁ፤ በደኅንነትም እንዲያርፉ አደርጋቸዋለሁ።