Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 9:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እንዲሁም ከእናንተ ጋራ ከነበሩት ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ፦ ከወፎች፣ ከቤት እንስሳት፣ ከዱር እንስሳት፣ ከእናንተ ጋራ ከመርከቧ ከወጡት በምድር ላይ ካሉት ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ጋራ ኪዳን እገባለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ይህም ከእናንተ ጋር ላሉትም ሕያው ነፍስ ላላቸው ሁሉ፥ ከእናንተ ጋር ከመርከብ ለወጡት አእዋፍ፥ ለእንስሳትም፥ ለምድር አራዊትም ሁሉ፥ ለየትኛውም የምድር አራዊት ሁሉ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እንዲሁም ሕይወት ካላቸው ፍጥረቶች ሁሉ፥ ማለትም ከወፎች፥ ከእንስሶችና ከአራዊት፥ ከአንተ ጋር ከመርከቡ ውስጥ ከወጡት ፍጥረቶችና ዘሮቻቸው ሁሉ ጋር ቃል ኪዳን እገባለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ከእ​ና​ንተ ጋር ላሉ​ትም፥ ሕያው ነፍስ ላላ​ቸው ሁሉ፥ ከእ​ና​ንተ ጋር ከመ​ር​ከብ ለወ​ጡት ለወ​ፎች፥ ለእ​ን​ስ​ሳ​ትም፥ ለም​ድር አራ​ዊ​ትም ሁሉ፥ ለማ​ን​ኛ​ውም ለም​ድር አራ​ዊት ሁሉ ይሆ​ናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ከእናንተ ጋር ከመርከብ ለወጡት ለወፎች፥ ለእንስሳትም ለምድር አራዊትም ሁሉ ለማንኛውም ለምድር አራዊት ሁሉ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 9:10
11 Referencias Cruzadas  

ታዲያ፣ እኔ ቀኝና ግራቸውን ለይተው መናገር የማይችሉ፣ ከአንድ መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሰዎችና አያሌ እንስሳት ለሚኖሩባት ለታላቋ ከተማ ለነነዌ ማዘን አይገባኝምን?”


እግዚአብሔር ለሁሉ ቸር ነው፤ ምሕረቱም በፍጥረቱ ሁሉ ላይ ነው።


እግዚአብሔር ኖኅንና በመርከቧ ውስጥ ከርሱ ጋራ የነበሩትን የዱርና የቤት እንስሳት ሁሉ ዐሰበ፤ በምድር ላይ ነፋስ እንዲነፍስ አደረገ፤ ውሃውም ጐደለ።


“እነሆ፤ ከእናንተና ከእናንተ በኋላ ከሚመጣው ዘራችሁ ጋራ ኪዳኔን እመሠርታለሁ፤


ከእንግዲህ ሕይወት ያለው ፍጡር ሁሉ በጥፋት ውሃ እንደማይጠፋ፣ ዳግመኛም ምድርን የሚያጠፋ ውሃ ከቶ እንደማይመጣ ከእናንተ ጋራ ኪዳን እገባለሁ።”


እንስሳቱ ሁሉ፣ ወፎችም፣ በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታት ሁሉ በየወገናቸው ከመርከቧ ወጡ።


በታማኝነት ዐጭሻለሁ፤ አንቺም እግዚአብሔርን ታውቂያለሽ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios