La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 48:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዮሴፍም ሁለቱን ልጆቹን ወሰደ፥ ኤፍሬምንም በቀኙ በእስራኤል ግራ፥ ምናሴንም በግራው በእስራኤል ቀኝ አደረገው፥ ወደ እርሱም አቀረባቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ዮሴፍ ሁለቱን ልጆቹን ይዞ ኤፍሬምን ከራሱ በስተቀኝ፣ ከእስራኤል በስተግራ፣ ምናሴን ደግሞ ከራሱ በስተግራ፣ ከእስራኤል በስተቀኝ በኩል አቀረባቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዮሴፍ ሁለቱን ልጆቹን ወስዶ ኤፍሬምን በቀኙ ለያዕቆብ በስተግራው በኩል፥ ምናሴን በግራው ለያዕቆብ በስተቀኝ በኩል አድርጎ አቀረበለት።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዮሴ​ፍም ሁለ​ቱን ልጆ​ቹን ወሰደ፤ ኤፍ​ሬ​ም​ንም በቀኙ በእ​ስ​ራ​ኤል ግራ፥ ምና​ሴ​ንም በግ​ራው በእ​ስ​ራ​ኤል ቀኝ አቆ​ማ​ቸው፤ ወደ አባ​ቱም አቀ​ረ​ባ​ቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዮሴፍም ሁለቱን ልጆቹን ወሰደ ኤፍሬምንም በቀኙ በእስራኤል ቀኝ አደረገው ወደ እርሱም አቀረባቸው።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 48:13
6 Referencias Cruzadas  

ዮሴፍም፥ “እግዚአብሔር መከራዬን ሁሉ፥ የአባቴንም ቤት እንድረሳ አድርጎኛል” በማለት የመጀመሪያ ልጁን ስም ምናሴ አለው።


የዮሴፍ ልጆች ምናሴና ኤፍሬም ናቸው፤ እነርሱም ዮሴፍ በግብጽ ምድር ከኦን ከተማ ካህን ከጶጢፌራ ሴት ልጅ ከአስናት የወለዳቸው ናቸው።


ዮሴፍም ከጉልበቱ ፈቀቅ አደረጋቸው፥ ወደ ምድርም በግምባሩ ሰገደ።


እስራኤልም ቀኝ እጁን ዘርግቶ በኤፍሬም ራስ ላይ አኖረው፥ እርሱም ታናሽ ነበረ፥ ግራውንም በምናሴ ራስ ላይ አኖረ፥ እጆቹንም አስተላለፈ፥ ምናሴ በኩር ነበርና።


በየወገናቸው የዮሴፍ ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ምናሴና ኤፍሬም።


በጎቹን በቀኙ ፍየሎቹን ደግሞ በግራው ያቆማቸዋል።