ዘፍጥረት 46:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮሴፍም ሠረገላውን አዘጋጀ፥ አባቱንም እስራኤልን ሊገናኘው ወደ ጌሤም ወጣ፥ ባየውም ጊዜ በአንገቱ ላይ ወደቀ፥ አቅፎትም ረጅም ጊዜ አለቀሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮሴፍ ሠረገላውን አዘጋጅቶ፤ አባቱን እስራኤልን ለመቀበል ወደ ጌሤም አመራ። ዮሴፍ አባቱ ዘንድ እንደ ደረሰ፣ ዐንገቱ ላይ ተጠምጥሞ ለረዥም ጊዜ አለቀሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮሴፍ አባቱን ለመገናኘት በሠረገላው ተቀምጦ ወደዚያ ሄደ፤ በተገናኙም ጊዜ ዮሴፍ በአባቱ አንገት ላይ ተጠምጥሞ ለብዙ ጊዜ አለቀሰ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮሴፍም ሰረገላውን አዘጋጀ፤ አባቱንም እስራኤልን ሊገናኘው ወደ ኤሮስ ከተማ ወጣ፤ በአየውም ጊዜ አንገቱን አቀፈው፤ ረዥም ጊዜም አለቀሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮሴፍም ሰረገላውን አዘጋጀ አባቱንም እስራኤልን ሊገናኘው ወደ ጌሤም ወጣ ባየውም ጊዜ በአንገቱ ላይ ወደቀ አቅፎትም ረጅም ጊዜ አለቀሰ። |
በማዕረግ ከእርሱ ሁለተኛ ሰው አድርጎ፥ በሠረገላ ላይ አስቀመጠው። ሰዎችም በፊቱ፥ “እጅ ንሡ” እያሉ ይጮኹ ነበር፤ በዚህ ሁኔታም በግብጽ ምድር ሁሉ ላይ ሾመው።