ዘፍጥረት 45:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም ከግብጽ አገርም ወጡ፥ ወደ ከነዓንም ምድር ከአባታቸው ከያዕቆብ ዘንድ ደረሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም ከግብጽ ወጥተው በከነዓን ምድር ወደሚኖረው ወደ አባታቸው ወደ ያዕቆብ መጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዮሴፍ ወንድሞች ከግብጽ ተነሥተው በከነዓን ወደሚኖረው አባታቸው ወደ ያዕቆብ ተመለሱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም ከግብፅ ሀገር ወጥተው ሄዱ፤ ወደ ከነዓንም ምድር ወደ አባታቸው ወደ ያዕቆብ ደረሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ሄዱ ከግብፅ አገርም ወጡ ወደ ከነዓንም ምድር ከአባታቸው ከያዕቆብም ዘንድ ደረሱ። |
እንዲህም ብለው ነገሩት፦ “ዮሴፍ ገና በሕይወቱ አለ፥ እርሱም በግብጽ ምድር ላይ ሁሉ ገዥ ሆኖአል።” ያዕቆብም ልቡ ደነገጠ፥ ሊያምናቸውም አልቻለም።