ዘፍጥረት 44:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቤቱ አዛዥም እንደ ደረሰባቸው፥ ልክ እንደተባለው ተናገራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቤቱ አዛዥም እንደ ደረሰባቸው፣ ልክ እንደ ተባለው ተናገራቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቤቱም አዛዥ ወደ ሰዎቹ እንደ ደረሰ ልክ እንደ ተባለው ነገራቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ሂዶ አገኛቸው፤ “ለምን እንዲህ አደረጋችሁ? ስለ አደረግሁላችሁ መልካም ነገር ለምን ክፉ ትከፍሉኛላችሁ? የጌታዬንስ የብር ጽዋ ለምን ሰረቃችሁኝ?” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ደርሰባቸው ይህንም ቃል ነገራቸው። |
እነሆ፥ ይህ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ኀዘን ለእንዴት ዓይነት ትጋት፥ ለእንዴት ዓይነት ራስን የማንጻት ጉጉት፥ ለእንዴት ዓይነት ቊጣ፥ ለእንዴት ዓይነት ፍርሃት፥ ለእንዴት ዓይነት ናፍቆት፥ ለእንዴት ዓይነት ቅንዓት፥ ለእንዴት ዓይነት ቅጣት እንዳደረሳችሁ ተመልከቱ! በዚህም ጉዳይ ንጹሓን መሆናችሁን በሁሉ ረገድ አስመስክራችኋል።