ዘፍጥረት 44:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንዱ በወጣበት በመቅረቱ፥ “በእርግጥ የአውሬ እራት ሆኖአል” አልሁ፤ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ይኸው የውሃ ሽታ ሆኖ ቀርቶአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንዱ በወጣበት በመቅረቱ፣ “በርግጥ የአውሬ እራት ሆኗል” አልሁ፤ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ይኸው የውሃ ሽታ ሆኖ ቀርቷል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእነርሱ አንዱ ከአሁን በፊት ተለይቶኛል፤ ከተለየኝ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ስላላየሁት ክፉ አውሬ በልቶት ይሆናል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንዱም ከእኔ ወጣ፤ አውሬ በላው አላችሁኝ፤ እስከ ዛሬም ገና አላየሁትም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንዱም ከእኔ ወጣ፦ አውሬ በላው አላችሁኝ እስከ ዛሬም አላየሁትም፤ |
አባታቸው ያዕቆብም፥ “ያለ ልጅ እኮ አስቀራችሁኝ፤ ዮሴፍ የለም፤ ስምዖንም የለም፤ አሁን ደግሞ ብንያምን ልትወስዱ ትፈልጋላችሁ፤ ኧረ ምን ጉድ ነው የመጣብኝ!” አላቸው።
ያዕቆብም፥ “ልጄ አብሮአችሁ ወደዚያ አይወርድም፤ ወንድሙ እንደሆን ሞቷል፤ የቀረው እርሱ ብቻ ነው። ይዛችሁት ስትሄዱ በመንገድ ላይ አደጋ ቢደርስበት፥ ሽበቴን በመሪር ኀዘን ወደ መቃብር ታወርዱታላችሁ” አላቸው።