ዘፍጥረት 43:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤልም፥ “ሌላ ወንድም አለን ብላችሁ ለዚያ ሰው በመንገር ለምን ይህን ችግር እንዲደርስብኝ አደረጋችሁ?” ሲል ጠየቃቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤልም፣ “ሌላ ወንድም አለን ብላችሁ ለዚያ ሰው በመንገር ለምን ይህን ችግር እንዲደርስብኝ አደረጋችሁ?” ሲል ጠየቃቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብም “ ‘ሌላ ወንድም አለን’ ብላችሁ ለሰውየው በመናገር ለምን ይህን ያህል መከራ አመጣችሁብኝ?” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስራኤልም አላቸው፥ “በእኔ ላይ ያደረጋችኋት ይህች ክፋት ምንድን ናት? በዚያውስ ላይ ሌላ ወንድም አለን ብላችሁ ለምን ነገራችሁት?” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስራኤልም አላቸው ለምን በደላችሁኝ? ለዚያውስ፦ ሌላ ወንድም አለን ብላችሁ ለምን ነገራችሁን? |
እነርሱም፥ “ሰውየው ስለ ራሳችንና ስለ ቤተሰባችን አጥብቆ ጠየቀን፤ እንደገናም ‘አባታችሁ አሁንም በሕይወት አለ? ሌላስ ወንድም አላችሁ’ ሲል ጠየቀን። እኛም ለጥያቄው መልስ ሰጠነው። ታድያ፥ ‘ወንድማችሁን ይዛችሁ ወደዚህ እንድትመጡ’ እንደሚል እንዴት ማወቅ እንችል ነበር?” ብለው መለሱለት።