ዘፍጥረት 43:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱን የማትልከው ከሆነ ግን እኛም ወደዚያ አንወርድም፤ ያም ሰው፥ ‘ወንድማችሁን ይዛችሁ ካልመጣችሁ ዳግመኛ ፊቴን አታዩም’ ብሎናል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱን የማትልከው ከሆነ ግን እኛም ወደዚያ አንወርድም፤ ያም ሰው፣ ‘ወንድማችሁን ይዛችሁ ካልመጣችሁ ዳግመኛ ፊቴን አታዩም’ ብሎናል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን የማትፈቅድልን ከሆነ ግን ‘ወንድማችሁን ይዛችሁ ካልመጣችሁ እፊቴ እንዳትቀርቡ’ ስላለን ወደዚያ አንሄድም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድማችንን ከእኛ ጋር ባትልከው ግን አንሄድም፤ ያ ሰው ‘ታናሽ ወንድማችሁን ከእናንተ ጋር ካላመጣችሁ ፊቴን አታዩም’ ብሎናልና።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያ ሰው፦ ወንድማችሁ ከእናንተ ጋር ካልሆነ ፊቴን አታዮም ብሎናልና። |
ታናሽ ወንድማችሁን ግን ይዛችሁ መምጣት አለባችሁ፤ በዚህም የተናገራችሁት ቃል እውነተኛነት ይረጋገጣል፤ እናንተም ከመሞት ትተርፋላችሁ።” እነርሱም ይህንኑ ለመፈጸም ተስማሙ።
ያዕቆብም፥ “ልጄ አብሮአችሁ ወደዚያ አይወርድም፤ ወንድሙ እንደሆን ሞቷል፤ የቀረው እርሱ ብቻ ነው። ይዛችሁት ስትሄዱ በመንገድ ላይ አደጋ ቢደርስበት፥ ሽበቴን በመሪር ኀዘን ወደ መቃብር ታወርዱታላችሁ” አላቸው።
‘መሄድ አንችልም፤ መሄድ የምንችለው ታናሽ ወንድማችን አብሮን ሲሄድ ብቻ ነው። ታናሽ ወንድማችንን ይዘን ካልሄድን በስተቀር፥ የሰውየውን ፊት ማየት አንችልም’ አልነው።