ዘፍጥረት 43:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ዮሴፍ ቤት አዛዥ ቀርበው፥ በቤቱ መግቢያ ላይ አነጋገሩት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ዮሴፍ ቤት አዛዥ ቀርበው፣ በቤቱ መግቢያ ላይ አነጋገሩት፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ወደ ቤቱ በር አጠገብ ሲደርሱ የቤቱን አዛዥ እንዲህ አሉት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ዮሴፍ ቤት አዛዥም ቀረቡ፤ በቤቱም ደጅ ተናገሩት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ዮሴፍ ቤት አዛዥ፥ ቀረቡ በቤቱ ደጅ ተናገሩት እንዲህም አሉት፦ |
ታናሽ ወንድማችሁን ግን ይዛችሁ መምጣት አለባችሁ፤ በዚህም የተናገራችሁት ቃል እውነተኛነት ይረጋገጣል፤ እናንተም ከመሞት ትተርፋላችሁ።” እነርሱም ይህንኑ ለመፈጸም ተስማሙ።
ዮሴፍ ብንያምን ከወንድሞቹ ጋር ባየው ጊዜ የቤቱን አዛዥ፥ “እነዚህን ሰዎች ወደ ቤት ይዘሃቸው ሂድ፤ ዛሬ ቀትር ላይ አብረውኝ ስለሚበሉ ፍሪዳ ተጥሎ ምሳ ይዘጋጅ” አለው።
የእስራኤልም ልጆች ወደ ዮሴፍ ቤት በመወሰዳቸው ፈሩ፤ እነርሱም፥ “ወደዚህ የመጣነው፥ ቀደም ሲል እዚህ መጥተን ስንመለስ በየስልቾቻችን ውስጥ ተመልሶ በተጨመረው ብር ሰበብ ነው። ሰውዬው ጥቃት ሊፈጽምብን፥ አስገድዶ ባሮቹ ሊያደርገንና አህዮቻችንን ሊቀማን ይፈልጋል” ብለው ሠጉ።
ደግሞም ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፦ “መጋቢ የሚያገለግለው አንድ ባለ ጠጋ ሰው ነበረ፤ ‘ይህ ሰው ያለህን ይበትናል፤’ የሚል ክስ በእርሱ ዘንድ አቀረቡ።