እርሱም በዘገየ ጊዜ እግዚአብሔር ስላዘነለት እነዚያ ሰዎች የእርሱን እጅ የሚስቱንም እጅ የሁለቱን የሴቶች ልጆቹንም እጅ ይዘው አወጡትና በከተማይቱ ውጭ አስቀመጡት።
ዘፍጥረት 43:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህን ያህል ባንዘገይ ኖሮ፥ እስካሁን ሁለት ጊዜ ደርሰን መመለስ በቻልን ነበር።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን ያህል ባንዘገይ ኖሮ፣ እስካሁን ሁለት ጊዜ ደርሰን መመለስ በቻልን ነበር።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ያህል ባንዘገይ ኖሮ እስከ አሁን ሁለት ጊዜ እዚያ ደርሰን መመለስ በቻልን ነበር።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባንዘገይስ ኖሮ አሁን ሁለተኛ ጊዜ በተመለስን ነበር።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባንዘገይስ ኖሮ አሁን ሁለተኛ ጊዜ በተመለስን ነበር። |
እርሱም በዘገየ ጊዜ እግዚአብሔር ስላዘነለት እነዚያ ሰዎች የእርሱን እጅ የሚስቱንም እጅ የሁለቱን የሴቶች ልጆቹንም እጅ ይዘው አወጡትና በከተማይቱ ውጭ አስቀመጡት።
ከዚህ በኋላ አባታቸው እስራኤል እንዲህ አላቸው፤ “ነገሩ እንዲህ ከሆነስ ይህን አድርጉ፤ ምድሪቱ ከምታፈራው ምርጥ ነገሮች ጥቂት በለሳን፥ ጥቂት ማር፥ ሽቱ፥ ከርቤ ተምርና ለውዝ በየስልቻችሁ ይዛችሁ ለዚያ ሰው እጅ መንሻ ውሰዱለት።
ስለ ልጁ ደኅንነት እኔ ራሴ ኀላፊ ነኝ፤ ስለ እርሱም በግል ተጠያቂ እሆናለሁ፤ እርሱንም በደኅና መልሼ ባላመጣውና እዚህ በፊትህ ባላቆመው ለዘለዓለም በደለኛ እኔ ልሁን።