እርሱም ወንድሞቹን፥ “ኧረ ብሬ ተመልሶልኛል፤ ይኸው ስልቻዬ ውስጥ አገኘሁት” አላቸው። ሁሉም ልባቸው በድንጋጤ ተሞልቶ እየተንቀጠቀጡ በመተያየት፥ “እግዚአብሔር ምን ሊያመጣብን ይሆን?” አሉ።
ዘፍጥረት 42:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በከነዓን ምድር ወዳለው ወደ አባታቸው ወደ ያዕቆብ ከደረሱ በኋላ፥ ያጋጠማቸውን ሁሉ እንዲህ ብለው ነገሩት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በከነዓን ምድር ወዳለው ወደ አባታቸው ወደ ያዕቆብ ከደረሱ በኋላ፣ ያጋጠማቸውን ሁሉ እንዲህ ብለው ነገሩት፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በከነዓን ወዳለው ወደ አባታቸው ወደ ያዕቆብ ተመለሱ፤ የደረሰባቸውን ሁሉ እንዲህ ብለው ነገሩት፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ አባታቸውም ወደ ያዕቆብ ወደ ከነዓን ምድር መጡ፤ የደረሰባቸውንም ነገር ሁሉ እንዲህ ብለው አወሩ፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ አባታቸውም ወደ ያዕቆብ ወደ ከነዓን ምድር መጡ የደረሰባቸውንም ነገር ሁሉ እንዲህ ብለው አወሩ፦ |
እርሱም ወንድሞቹን፥ “ኧረ ብሬ ተመልሶልኛል፤ ይኸው ስልቻዬ ውስጥ አገኘሁት” አላቸው። ሁሉም ልባቸው በድንጋጤ ተሞልቶ እየተንቀጠቀጡ በመተያየት፥ “እግዚአብሔር ምን ሊያመጣብን ይሆን?” አሉ።
እንዲህም ብለው ነገሩት፦ “ዮሴፍ ገና በሕይወቱ አለ፥ እርሱም በግብጽ ምድር ላይ ሁሉ ገዥ ሆኖአል።” ያዕቆብም ልቡ ደነገጠ፥ ሊያምናቸውም አልቻለም።