ከዚህ በኋላ ግን በተከታታይ ሰባት የራብ ዓመታት ይሆናሉ። የራቡ ዘመን አገሪቱን እጅግ ስለሚጐዳት፥ በግብጽ የነበረው ያለፈው የጥጋብ ዘመን ሁሉ ጨርሶ አይታወስም።
ዘፍጥረት 41:51 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮሴፍም፥ “እግዚአብሔር መከራዬን ሁሉ፥ የአባቴንም ቤት እንድረሳ አድርጎኛል” በማለት የመጀመሪያ ልጁን ስም ምናሴ አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮሴፍም፣ “እግዚአብሔር መከራዬን ሁሉ፣ የአባቴንም ቤት እንድረሳ አድርጎኛል” በማለት የመጀመሪያ ልጁን ስም ምናሴ አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮሴፍ “እግዚአብሔር የደረሰብኝን መከራና ዘመዶቼን እንድረሳ አደረገኝ” በማለት የመጀመሪያ ልጁን ምናሴ ብሎ ጠራው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮሴፍም የበኵር ልጁን ስም ምናሴ ብሎ ጠራው፤ እንዲህ ሲል፥ “እግዚአብሔር መከራዬን ሁሉ የአባቴንም ቤት እንድረሳ አደረገኝ፤” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮሴፍም የበኵር ልጅን ስም ምናሴ ብሎ ጠራው እንዲህ ሲል እግዚአብሔር መከራዬን ሁሉ የአባቴንም ቤት አስረስኝ |
ከዚህ በኋላ ግን በተከታታይ ሰባት የራብ ዓመታት ይሆናሉ። የራቡ ዘመን አገሪቱን እጅግ ስለሚጐዳት፥ በግብጽ የነበረው ያለፈው የጥጋብ ዘመን ሁሉ ጨርሶ አይታወስም።
ጥቂት ጊዜ ካለፈ በኋላ “አባትህ ታሞአል” ተብሎ ለዮሴፍ ተነገረው፤ ስለዚህ ዮሴፍ ሁለቱን ልጆቹን ምናሴንና ኤፍሬምን ይዞ ያዕቆብን ለማየት ሄደ።
አሁንም እኔ ወደ አንተ ከመምጣቴ በፊት በግብጽ ምድር የተወለዱልህ ሁለቱ ልጆችህ ለእኔ ይሁኑ፥ ኤፍሬምና ምናሴ ለእኔ እንደ ሮቤልና እንደ ስምዖን ናቸው።
እንዲሁም በምድር ላይ የተባረከ በእውነት አምላክ ይባረካል፥ በምድርም ላይ የማለ በእውነት አምላክ ይምላል፤ ምክንያቱም የቀድሞው ጭንቀት ተረስቶአል፥ ከዓይኔም ተሰውሮአል።
ለላሞች በኩር ግርማ ይሆናል፥ ቀንዶቹ አንድ ቀንድ እንዳለው ናቸው፥ በእነርሱ እስከ ምድር ዳርቻ ያሉትን አሕዛብ ሁሉ ይወጋል፥ የኤፍሬም እልፍ አእላፋት፥ የምናሴም አእላፋት እነርሱ ናቸው።”
የዮሴፍ ልጆች ምናሴና ኤፍሬም ሁለት ነገዶች ነበሩ፤ ለሌዋውያንም ከሚቀመጡባቸው ከተሞች ለእንሰሶቻቸውና ለከብቶቻቸውም ከሚሆን ማሰማርያ በቀር በምድሩ ውስጥ ድርሻ አልሰጡአቸውም።
ለምናሴ ነገድ ዕጣው ይህ ነው፤ የዮሴፍ በኩር እርሱ ነውና። የምናሴም በኩር የገለዓድ አባት ማኪር ብርቱ ተዋጊ ስለ ነበረ ገለዓድንና ባሳንን ወረሰ።