ዘፍጥረት 40:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእንጀራ ቤት አዛዡን ግን ልክ ዮሴፍ እንደ ተረጐመላቸው ሰቀለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእንጀራ ቤት አዛዡን ግን ልክ ዮሴፍ እንደ ተረጐመላቸው ሰቀለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእንጀራ ቤት ኀላፊውን ግን እንዲሰቀል አደረገው፤ ሁሉም ነገር ዮሴፍ የእያንዳንዳቸውን ሕልም እንደ ተረጐመው ሆነ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእንጀራ አበዛዎቹንም አለቃ በዕንጨት ላይ ሰቀለው፤ ዮሴፍ እንደ ተረጐመላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእንጀራ አበዛዎቹንም አለቃ ሰቀለው ዮሴፍ እንደተረጎመላቸው። |
እነርሱም “ሁለታችንም ሕልም አየን፤ ነገር ግን የሚተረጉምልን ሰው አጣን” ሲሉ መለሱለት። ዮሴፍም፥ “ሁልጊዜስ ቢሆን የሕልም ትርጓሜ ከእግዚአብሔር የሚገኝ አይደለምን? እስቲ ያያችሁትን ሕልም ንገሩኝ” አላቸው።