ዘፍጥረት 40:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተክሏም ሦስት ሐረጎች ነበሯት፤ ወዲያው አቈጥቊጣ አበበች፤ ዘለላዎቿም ተንዠርግገው በሰሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተክሏም ሦስት ሐረጎች ነበሯት፤ ወዲያው አቈጥቍጣ አበበች፤ ዘለላዎቿም ተንዠርግገው በሰሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተክሉም ላይ ሦስት ሐረጎች ነበሩ፤ ቅጠሉ ለምልሞ ወዲያው አበባ አወጣ፤ የወይን ዘለላውም ወዲያው በሰለ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሐረጉም ሦስት ቅርንጫፎች ወጡ፤ እርስዋም ቅጠልና አበባ አወጣች፤ ዘለላም አንጠለጠለች፤ የዘለላዋም ፍሬ በሰለ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሕልሜ የወይን ዛፍ በፊቴ ሆና አየሁ በዛፊቱም ሦስት አረግ አለበት እርስዋም ቅጠልን አበባ አወጣች፥ ዘለላም አንጠለጠለች፥ |
እንዲህም ሆነ፤ በማግስቱ ሙሴ ወደ ምስክሩ ድንኳን ውስጥ ገባ፤ እነሆም፥ ለሌዊ ቤት የሆነው የአሮን በትር አቈጥቁጦ፥ እምቡጥም አውጥቶ፥ አበባም አብቦ፥ የበሰለ ለውዝም አፍርቶ ነበር።