ዘፍጥረት 39:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮሴፍ በእርሱ ዘንድ ሞገስ አገኘ፤ የቅርብ አገልጋዩም ሆነ። ጲጥፋራ በቤቱ ላይ ሾመው፤ ያለውንም ሀብት ሁሉ በኀላፊነት ሰጠው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮሴፍ በርሱ ዘንድ ሞገስ አገኘ፤ የቅርብ አገልጋዩም ሆነ። ጲጥፋራ በቤቱ ላይ ሾመው፤ ያለውንም ሀብት ሁሉ በኀላፊነት ሰጠው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጶጢፋር ዮሴፍን ወደደው፤ የቅርብ አገልጋዩም አደረገው፤ በቤቱ ላይ አዛዥነትን፥ በንብረቱም ሁሉ ላይ ኀላፊነትን ሰጠው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮሴፍም በጌታው ፊት ሞገስን አገኘ፤ እርሱንም ደስ ያሰኘው ነበር፤ በቤቱም ላይ ሾመው፤ ያለውንም ሁሉ በእጁ ሰጠው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮሴፍም በጌታው ፊት ሞገስን አገኘ እርሱንም ያገለግለው ነበር በቤቱም ላይ ሾመው ያለውንም ሁሉ በእጁ ሰጠው። |
እነሆ ባርያህ በፊትህ ሞገስን አግኝቶአል፥ ነፍሴን ለማዳን ያደረግህልኝን ምሕረትህንም አብዝተሃል፥ ክፉ እንዳያገኘኝና እንዳልሞት ወደ ተራራ ሸሽቼ አመልጥ ዘንድ አልችልም፥
ያዕቆብም አለ፥ “እንደዚህ አይሁን፥ ነገር ግን በፊትህ ሞገስን አግኝቼ እንደሆንሁ፥ እጅ መንሻዬን ተቀበለኝ፥ የእግዚአብሔርን ፊት እንደሚያይ ፊትህን አይቼአለሁና፥ በቸርነትም ተቀብለኸኛልና።
እርሱ ግን ፈቃደኛ አልሆነም፤ እንዲህም አላት፤ “ጌታዬ ያለውን ሁሉ በኀላፊነት ስለ ሰጠኝ፥ በቤቱ ውስጥ ስላለው ሁሉ ምንም የሚያውቀው ነገር የለም።
የሠረገላዎቹ እኩሌታ ኀላፊ የሆነ ዚምሪ ተብሎ የሚጠራ ከጦር መኰንኖቹ አንዱ በንጉሡ ላይ ዐደመ፤ አንድ ቀን ኤላ በቲርጻ ከተማ የቤተ መንግሥቱ ኀላፊ በሆነው አርጻ ተብሎ በሚጠራው ባለሟሉ ቤት ብዙ መጠጥ ጠጥቶ ሰክሮ ነበር።
በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ኤጲስ ቆጶሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።