ዘፍጥረት 36:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዔሳው ልጅ የረዑኤል ልጆች እነዚህ ናቸው፥ ናሐት አለቃ፥ ዘራሕ አለቃ፥ ሻማ አለቃ፥ ሚዛህ አለቃ፥ በኤዶም ምድር የረዑኤል ልጆች አለቆች እነዚህ ናቸው፤ እነዚህም የዔሳው ሚስት የባሴማት ልጆች ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዔሳው ልጅ ራጉኤል ልጆች፦ አለቃ ናሖት፣ አለቃ ዛራ፣ አለቃ ሣማና አለቃ ሚዛህ፤ እነዚህ በኤዶም ምድር ከራጉኤል የተገኙ የነገድ አለቆች፣ የዔሳው ሚስት የቤሴሞት የልጅ ልጅ ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዔሳው ልጅ የረዑኤል ነገድ አለቆች፦ ናሐት፥ ዘራሕ፥ ሻማና ሚዛ ሲሆኑ እነዚህ በኤዶም የረዑኤል ነገድ አለቆች ናቸው፤ እነርሱም ዔሳው ከሚስቱ ከባሴማት የወለዳቸው ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዔሳው ልጅ የራጉኤል ልጆች መሳፍንት እነዚህ ናቸው፤ ናሖት መስፍን፥ ዛራ መስፍን፥ ሲን መስፍን፥ ሞዛህ መስፍን፤ በኤዶም ምድር የራጉኤል ልጆች መሳፍንት እነዚህ ናቸው፤ እነዚህም የዔሳው ሚስት የቤሴሞት ልጆች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዔሳው ልጅ የራጉኤል ልጆች እነዚህ ናቸው ናሖት አለቃ ዛራ አለቃ ሣማ አለቃ ሚዛህ እለልቃ በኤዶም ምድር የራጉኤል ልጆች አለቆች እነዚህ ናቸው እነዚህም የዔሳው ሚስት የቤሴሞት ልጆች ናቸው። |
የዔሳው ሚስት የኦሆሊባማ ልጆች እነዚህ ናቸው፦ የዑሽ አለቃ፥ ያዕላም አለቃ፥ ቆሬ አለቃ፥ የዔሳው ሚስት የዓና ልጅ የኦሆሊባማ አለቆች እነዚህ ናቸው።