ያዕቆብም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር በተነጋገረበት ቦታ የድንጋይ ዐምድ አኖረ፤ የመጠጥ መሥዋዕትንም በእርሱ ላይ አፈሰሰ፥ ዘይትንም አፈሰሰበት።
ዘፍጥረት 35:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብም በመቃብርዋ ላይ ሐውልት አቆመ፥ እርሱም እስከ ዛሬ የራሔል የመቃብርዋ ሐውልት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብም በራሔል መቃብር ላይ ሐውልት አቆመ፤ እስከ ዛሬም የራሔል መቃብር ምልክት ይኸው ሐውልት ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብም በራሔል መቃብር ላይ ለመታሰቢያዋ የሚሆን የድንጋይ ሐውልት አቆመ። ይህም ሐውልት እስከ ዛሬ ድረስ የራሔልን መቃብር ያመለክታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብም በመቃብርዋ ላይ ሐውልት አቆመ፤ እርስዋም እስከ ዛሬ የራሔል የመቃብርዋ ሐውልት ትባላለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብም በመቃብርዋ ላይ ሐውልት አቆመ እርሱም እስከ ዛሬ የራሔል የመቃብርዋ ሐውልት ነው። |
ያዕቆብም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር በተነጋገረበት ቦታ የድንጋይ ዐምድ አኖረ፤ የመጠጥ መሥዋዕትንም በእርሱ ላይ አፈሰሰ፥ ዘይትንም አፈሰሰበት።
እኔም ፓዳን በመጣሁ ጊዜ፥ ወደ ኤፍራታ ለመግባት ጥቂት መንገድ ቀርቶኝ ሳለሁ፥ ራሔል በከነዓን ምድር ሞተችብኝ፥ በዚያም በኤፍራታ መንገድ ላይ፥ ቀበርኋት፥ እርሷም ቤተልሔም ናት።
ዛሬ ከእኔ ተለይተህ ስትሄድ፥ በብንያም ወሰን ላይ በምትገኘው ጼልጻህ በተባለች ስፍራ በራሔል መቃብር አጠገብ ሁለት ሰዎች ታገኛለህ። እነርሱም፥ ‘የምትፈልጋቸው አህዮች ተገኝተዋል፤ አሁን አባትህ ስለ አህዮቹ ማሰቡን ትቶ፥ ስለ ልጄ ምን ባደርግ ይሻለኛል?’ እያለ በመጨነቅ ላይ ነው” ይሉሃል።