ዘፍጥረት 34:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እነዚህ ሰዎች በእኛ ዘንድ የሰላም ሰዎች ናቸው፥ በምድራችን ይቀመጡ፥ ይነግዱባትም፥ እነሆም ምድሪቱ ሰፊ ናት፥ ሴቶች ልጆቻቸውን እንውሰድ፥ ለእነርሱም ሴቶች ልጆቻችንን እንስጥ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም አሏቸው፤ “እነዚህ ሰዎች ወዳጆቻችን ናቸው፤ በአገራችን እንዲኖሩ፣ ተዘዋውረውም እንዲነግዱ እንፍቀድላቸው፤ ምድሪቱ እንደሆን ለእኛም ለእነርሱም ትበቃለች። ሴቶች ልጆቻቸውን እናገባለን፤ እነርሱም የእኛን ሴቶች ያገባሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እነዚህ ሰዎች ከእኛ ጋር የሚኖሩት በሰላም ነው፤ በምድሪቱ ላይ አብረውን ይቀመጡ፤ በነጻም ይዘዋወሩባት፤ እነሆ፥ ምድሪቱ ለእኛም ለእነርሱም ትበቃናለች፤ የእነርሱን ሴቶች ልጆች እናግባ፤ የእኛንም ሴቶች ልጆች እንዳርላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እነዚህ ሰዎች በእኛ ዘንድ የሰላም ሰዎች ናቸው፤ በምድራችን ይቀመጡ፤ ይነግዱባትም፤ እነሆም፥ ምድሪቱ ሰፊ ናት፤ ሴቶች ልጆቻቸውን ለሚስትነት እንውሰድ፤ ለእነርሱም ሴቶች ልጆቻችንን እንስጥ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገሩ፦ እነዚህ ሰዎች በእኛ ዘንድ የሰላም ሰዎች ናቸው በምድራችን ይቀመጡ ይነግዱባትም እነሆም ምድሪቱ ሰፊ ናት ሴቶች ልጆቻቸውን እንውሰድ ለእነርሱም ሴቶች ልጆቻቸንን እንስጥ |
ነገር ግን አንድ ሕዝብ ሆነን ከእኛ ጋር ይቀመጡ ዘንድ በዚህ ነገር ብቻ እሺ ይሉናል፥ እርሱም እነርሱ እንደ ተገረዙ ወንዶቻችንን ሁሉ ብንገርዝ ነው።
ነገር ግን ታናሽ ወንድማችሁን ወደ እኔ አምጡት። በዚያንም ጊዜ ታማኝ ሰዎች እንጂ ሰላዮች አለመሆናችሁን ዐውቃለሁ፤ ወንድማችሁንም መልሼ እሰጣችኋለሁ፤ እናንተም በምድሪቱ እንደ ልብ ለመዘዋወር ትችላላችሁ።’”