ዘፍጥረት 34:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴቶች ልጆቻችንንም እንሰጣችኋለን፥ የእናንተንም ሴቶች ልጆች እንወስዳለን፥ አንድ ሕዝብም ሆነን ከእናንተ ጋር እንኖራለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያ በኋላ ሴቶች ልጆቻችንን እንድርላችኋለን፤ ዐብረን እንኖራለን፤ አንድ ሕዝብም እንሆናለን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲህ ከሆነ እናንተ የእኛን ሴቶች ልጆች ታገባላችሁ፤ እኛም የእናንተን ሴቶች ልጆች እናገባለን፤ አንድ ሕዝብ ሆነንም አብረን እንኖራለን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴቶች ልጆቻችንንም እንሰጣችኋለን፤ የእናንተንም ሴቶች ልጆች ለሚስትነት እንወስዳለን፤ አንድ ሕዝብም ሆነን ከእናንተ ጋር እንኖራለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴቶች ልጆች እንወስዳለን አንድ ሕዝብም ሆነን ከእናንተ ጋር እንኖራለን። |