ዘፍጥረት 31:39 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አውሬ የሰበረውን አላመጣሁልህም ነበር፥ እኔው ራሴ ስለ እርሱ እከፍልህ ነበርሁ፥ በቀን ሆነ በሌሊት ቢሰረቅ፥ ያን ከእጄ ትፈልግ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አውሬ የሰበረውንም ቢሆን እተካ ነበር እንጂ፣ ትራፊውን ለምልክትነት አምጥቼ አላውቅም፤ በቀንም ሆነ በሌሊት የተሰረቁትን ሁሉ ስታስከፍለኝ ኖረሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከበጎችህ አንዱን አውሬ ሲበላው ወዲያው እከፍልህ ነበር እንጂ የእኔ ስሕተት ያለመሆኑን ለማስረዳት ወደ አንተ አምጥቼው አላውቅም፤ በቀንም ቢሆን በሌሊት የተሰረቀ እንስሳ ቢኖር ታስከፍለኝ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አውሬ የሰበረውንም አላመጣሁልህም ነበር፤ በቀንም ሆነ በሌሊት የተሰረቀ ቢኖር ከእኔ እከፍልህ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ስለ እርሱ እከፍልህ ነበርሁ በቀንም በሌሊትም የተሰረቀውን ከእጄ ትሻው ነበርህ። |
አንድ ሰው ለባልንጀራው አህያ ወይም በሬ ወይም በግ ወይም ሌላ እንስሳ እንዲጠብቅለት በአደራ ቢሰጥ፥ ማንም ሳያይ ቢሞት ወይም ቢጎዳ ወይም ቢማረክ፥